Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር ታዘባቸው 'ትምህርቱን ከአራተኛ ዓመት እንዲቀጥል' ተወስኖለታል፡፡ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በህክ | ATC NEWS

ዶ/ር ታዘባቸው "ትምህርቱን ከአራተኛ ዓመት እንዲቀጥል" ተወስኖለታል፡፡

ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በህክምና የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው ዶ/ር ታዘባቸው ውዴ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማህፀንና ፅንስ ሬዚደንትነት ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቷል፡፡

ዶ/ር ታዘባቸው ስፔሻላይዜሽን ትምህርቱን ለማጠናቀቅ ሁለት ወራት ሲቀረው በአንደኛው አይኑ ላይ ባለበት መሸዋረር ምክንያት ትምህርቱን እንዲያቆም መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡ ወደሌላ የትምህርት ክፍል ተዘዋውሮ ከአንደኛ ዓመት እንዲጀምር መወሰኑም አይዘነጋም፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ እና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የባለሙያዎች ቡድን በማቋቋም የዶ/ር ታዘባቸውን ቅሬታ ሲመረምር ቆይቷል፡፡

የባለሙያዎች ቡድን የቀረቡለትን መረጃና ማስረጃዎች ከመረመሩና እንደገና የማጣራት ሥራ ካከናወኑ በኋላ ዶ/ር ታዘባቸው ወደ ትምህርቱ እንዲመለስ የውሳኔ ምክረ ሃሳባቸውን ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ አቅርበዋል።

የዩኒቨርስቲው ቦርድም የባለሙያዎቹን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ዶ/ር ታዘባቸው ትምህርቱን ከአራተኛ ዓመት እንዲቀጥል ወስኗል፡፡

ዶ/ር ታዘባቸው ትምህርቱን አቋርጦ በቆየበት ወቅት ድጋፍ ላደረጉለትና ውሳኔውን በመቃወም ለተሟገቱለት አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡ #Hakim


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news