Get Mystery Box with random crypto!

በመጪዎቹ በዓላት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ካጋጠመ በፍጥነት የሚጠግን ግብረ ኃይል ተዘጋጅቷል - | ATC NEWS

በመጪዎቹ በዓላት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ካጋጠመ በፍጥነት የሚጠግን ግብረ ኃይል ተዘጋጅቷል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በመጪዎቹ በዓላት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር ካጋጠመ በፍጥነት የሚጠግን ግብረ-ኃይል መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ።

የፋሲካና የዒድ አልፈጥር በዓላት በሚከበሩባቸው ቀናት ሊያጋጥም የሚችለውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር ለመፍታት በቂ ዝግጅት ስለመደረጉ አገልግሎቱ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር መላኩ ታዬ ተቋሙ ያደረገውን ቅድመ-ዝግጅት በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት ለበዓላቱ አከባበር የኃይል መቆራረጥ ችግር እንዳይከሰት አስቀድሞ የማስተካከያ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

የኃይል መቆራረጥ ችግር ቢያጋጥም እንኳን በአስቸኳይ ጥገና የሚያደርግ የባለሙያዎች ግብረ-ኃይል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።



@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news