Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ ፍቃድ ለመስጠት ምዝገባ ማካ | ATC NEWS

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ ፍቃድ ለመስጠት ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል።

ባለሥልጣኑ ከህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ለሚከፈቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠት ማቆሙ ይታወቃል።

ባለሥልጣኑ አዲስ ፈቃድ የሚያገኙ ተቋማት ማሟላት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች የሚደነግጉ መመሪያዎች ዝግጅት ማጠናቀቁን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የተሻሻሉት መመሪያዎቹ ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም ፈቃድ የነበራቸውን ጨምሮ ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉ እንደ አዲስ ምዝገባ መፈጸም እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

ምዝገባው በዘንድሮ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን በ2016 ዓ.ም አዲስ ፍቃድና የእድሳት አገልግሎት መስጠት ሊጀመር እንደሚችል ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ 360 የሚጠጉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን መረጃ ያሳያል።

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news