Get Mystery Box with random crypto!

የተወርዋሪ ኮከብ አና የትክክለኞቹ ኮከቦች ልዩነት ተወርዋሪ ኮከቦች በተለመዶ ወደ ምድር ሲመጡ የ | አስትሮኖሚ 🚀🔭

የተወርዋሪ ኮከብ አና የትክክለኞቹ ኮከቦች ልዩነት

ተወርዋሪ ኮከቦች በተለመዶ ወደ ምድር ሲመጡ የሚታዩ ነገሮች ሲሆን ካሁን አሁን ወደቁ ብለን ስናስብ ተመልሰው በቅፅበት ይጠፍሉ ለማንኛው ኮከቦች ማለት አደሉም ጭራሽ የማይገናኙ ነገሮች ናቸው እንዚህ ተወርዋሪ ኮከቦች የሚገኙት በኛው ሶላር ሲስተም ውስጥ ሲሆን ትክክለኞቹ ከዋክብት ግን የሚገኙት ከኛ ሶላር ሲስተም ውጭ ነው

ተወርዋሪ ኮከቦች ከክዋክብት አንፃር እጅግ ትንሽ ነገሮች ናቸው ወይም የተሰባበሩ ድንጋዮች ናቸው እንዚህ ነገሮች ወደ ምድራች የሚወድቁ ሲሆን ምንም አይነት ጉዳት አያስከትሉም ምክንያቱም በጣም ትንሽ እና የመሬት ከባቢ አየር ውስጥ እንደገቡ ተቃጥለው የሚጠፉ ነገሮች ናቸው እኛ ከመሬት ላይ የምናየውም ይሄንኑ ነው ማለትም ሲቃጠሉ ነገረ ግን ኮከብ ይመስላሉ እንጂ አደሉም

ተወርዋሪ ኮከቦች የሚመጡት ከማርስ አጠገብ ከሚገኘው ከድንጋዮች ጥርቅም ነው በዚህ ቦታ እጅግ ብዙ ድንጋዮች በመሰባሰብ ፀሐይን የሚዞሯት ሲሆን ድንገት ከእሽክርክሪታቸው እየወጡ ወደ ፕላኔቶች ይወድቃሉ ከፕላኔቶች አንዷም የኛዋ ምድር ስትሆን በየአመቱ እጅግ በብዙ ተወርዋሪ ኮከቦች ትመታለች ግን ምንም ጉዳት ሳያስከትሉ ታቃጥላቸዋለ
@astronomy21bk