Get Mystery Box with random crypto!

#በደቡብ ክልል በወልቂጤ ከተማ በመጠጥ ቤት በተነሳ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ!!! | አዲስ መረጃ

#በደቡብ ክልል በወልቂጤ ከተማ በመጠጥ ቤት በተነሳ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ!!!

@በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በመጠጥ ቤት ዉስጥ በተነሳ ግጭት በስለት የተወጉ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አምስት ሰዎች መቁሰላቸዉን በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@በከተማው ረካቦቃ ቀበሌ ግንቦት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ በመጠጥ ቤት ውስጥ ሲዝናኑ በነበሩ ወጣቶች መካከል በተነሳ የቡድን ፀብ በስለት የተወጉ ሁለት ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ አምስት ሰዎች መቁሰላቸዉና በህክምና ተረድተዉ በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸዉ ተገልጿል።

@ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት አላቸዉ ሲል በወንጀሉ የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር አውሏል። የሟቾች አስክሬን ወደ ሆስፒታል ተልኮ እንዲመረመር መደረጉና በግድያ ወንጀል የተሳተፉን በመለየት ለፍርድ ማቅረብ እንዲቻል ፖሊስ የምርመራና የማጣራቱ ስራ መጀመሩን ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።