Get Mystery Box with random crypto!

የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የመስጊድ ማፍረስ እንዲያስቆም ጥሪ ቀረበ አምባ ዲ | አዲስ መረጃ

የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የመስጊድ ማፍረስ እንዲያስቆም ጥሪ ቀረበ

አምባ ዲጂታል፤ ሰኞ ግንቦት 28፣ 2015 – ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሚመሩት የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ውስጥ ኦሮሚያ ክልል የሚካሄደውን የመስጊድ ማፍረስ እንዲያስቆም ጥሪ ያቀረበው በአገሪቱ ለመብቶች የሚታገለው የአሜሪካ ኢስላሚክ ሪሌሽንስ ካውንስል ነው፡፡

ካውንስሉ ለባይደን አስተዳደር በጻፈው ደብዳቤ፤ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ 19 መስጊዶች መፍረሳቸውን የክልሉን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጠቅሶ መረጃ አስፍሯል፡፡ የካውንስሉ ደብዳቤ የአሜሪካ መንግሥት መስጊዶች እንዳይፈርሱ እርምጃ እንዲወስድ ተጠይቆበታል፡፡