Get Mystery Box with random crypto!

ሶስተኛው ዙር የትህነግ ወረራ! ደሳለኝ ጫኔ (ፒኤችዲ) የትግሬ ወራሪ ሰራዊት በአማራ ሕዝብ ላይ | አሥራት ሚዲያ Asrat Media ®🇪🇹

ሶስተኛው ዙር የትህነግ ወረራ! ደሳለኝ ጫኔ (ፒኤችዲ)

የትግሬ ወራሪ ሰራዊት በአማራ ሕዝብ ላይ በከፈተው ሶስተኛ ዙር ወረራ ምክንያት ዛሬም የራያ ቆቦ አካባቢ ሕዝብ በጠላት እጅ ወድቆ ሰቆቃ እንዲፈፀምበት፣ የሀብት ንብረት ዘረፋና ውድመት እየደረሰበት ነው። ትህነግ መራሹ ወራሪ የጥፋት ኃይል ወደ አፋር ክልልም ወረራውን አስፋፍቷል።

የአማራ ክልል መንግስት እና የፌደራል መንግስቱ አስፈላጊውን የሀይል ስምሪት እና የተቀናጀ አመራር በመስጠት የትሕነግን ወረራ የመመከት ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ አቀርባለሁ።

አሁንም ትህነግ የሚያሰማራው የሕዝብ ማዕበል ከመደበኛ የፀጥታ መዋቅሩ አቅም በላይ እንደሚሆን አመላካች ሁኔታዎች እንደሚኖሩ ግምት የሚወሰድ ከሆነ አስቀድሞ መወሰን ያለባቸው ውሳኔዎች ሳይረፍድ መወሰን አለባቸው። በኋላ የሚደረደር አንድ ሺህ አንድ ሰበብ የሕዝባችን ዳግም ውድመት አያስቀርምና ከወዲሁ ሁሉም የድርሻውን ይወጣ ዘንድ እጠይቃለሁ።

  ደሳለኝ ጫኔ (ፒኤችዲ)
@asrat_news
@asrat_news