Get Mystery Box with random crypto!

የሰማይ ደጆች ይከፈታሉ፥ የጀሃነም ደጆች ይዘጋሉ” ማለት 'በዚህ ወር የሚሞት ሁሉ እሳት አይገባም፥ | 📚እጅግ አስገራሚ ነገር ነው (ማሜ)🌴

የሰማይ ደጆች ይከፈታሉ፥ የጀሃነም ደጆች ይዘጋሉ” ማለት "በዚህ ወር የሚሞት ሁሉ እሳት አይገባም፥ ሁሉም ጀነት ይገባል" ማለት ሳይሆን የወሩን ድባብ ታላቅነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፥ በዚህ ወር “የሰማይ ደጆች ይከፈታሉ” ማለት "ሌላውን 11 ወራት ዝግ ነበር" ማለት እንዳልሆነ ሁሉ፥ ሙእሚን ዘርፈ-ብዙ እና መጠነ-ሰፊ የአምልኮ ተግባራትን በማከናወን ወደ አሏህ የሚቀርቡበትን የጸጋ ወር ለማመልከት የተገለጸ ፈሊጣዊ አገላለጽ ነው። ለምሳሌ ሙሥሊም በሳምንት ውስጥ ሁለት ቀናት የሡናህ አጥዋማት ይፆማል፥ እነርሱም ሰኞ እና ሐሙስ ናቸው። ሰኞ እና ሐሙስ የጀነት ደጃፎች በአሏህ ላይ ምንም ነገር ላላሻረከ ሁሉ ይከፈታል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 43
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም እንዲህ አሉ፦ ”የጀነት ደጃፎች በአላህ ላይ ምንም ነገር ላላሻረከ ሁሉ ሰኞ ቀን እና ሐሙስ ቀን ይከፈታል፥ አንድ ሰው በውስጡ መራራነት በወንድሙ ላይ ካለበት በስተቀር”። እንዲህም ይባላል፦ “በሁለቱ መካከል ዕርቅ እስኪሆን ድረስ አጢኑ፣ በሁለቱ መካከል ዕርቅ እስኪሆን ድረስ አጢኑ፣ በሁለቱ መካከል ዕርቅ እስኪሆን ድረስ አጢኑ”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ تُفْتَحُ أَبْوَابُ الْجَنَّةِ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَيَوْمَ الْخَمِيسِ فَيُغْفَرُ لِكُلِّ عَبْدٍ لاَ يُشْرِكُ بِاللَّهِ شَيْئًا إِلاَّ رَجُلاً كَانَتْ بَيْنَهُ وَبَيْنَ أَخِيهِ شَحْنَاءُ فَيُقَالُ أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا

የጀነት ደጃፎች ሰኞ ቀን እና ሐሙስ ቀን ክፍት የሆነው ቂም ወይም ጥላቻ በሙሥሊም ወንድሙ ላይ በልቡ ላልቋጠረ ሙሥሊም ነው። ሰኞ እና ሐሙስ ሳምንታዊ መጠነ-ሰፊ የአምልኮ ጊዜ ለማመልከት እንጂ ሌላውን የአዘቦት ቀናት ሥራዎች አይቀርቡም ወይም አሏህ ይቅር አይልም አሊያም የጀነት ደጃፎች አይከፈቱም ማለትን እንደማያሲዝ ሁሉ በረመዷን ወር “የሰማይ ደጆች ይከፈታሉ” ማለት "ሌላውን 11 ወራት ዝግ ነበር" ማለት አይደለም፥ የወሩን ድባብ ታላቅነት የሚያሳይ ነው።

“አሏሁ አዕለም” اَللّٰهُ أَعْلَم‎

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም