Get Mystery Box with random crypto!

ጀሚል የሚባሉ ቆንጆ ዉብ አይናማ ከላማቸው ደሞ ለዛ ያለው ግርማ ሀላቸው ያማረ ንግግር አዋቂ እኮ | Art on as sunnah

ጀሚል የሚባሉ ቆንጆ ዉብ አይናማ
ከላማቸው ደሞ ለዛ ያለው ግርማ
ሀላቸው ያማረ ንግግር አዋቂ
እኮን ለሙእሚኑ ካፊር አስደናቂ
ሙፍቲ እኮ ናቸው ኸይርን አሳአዋቂ
ሚወክለን የለ የሚሆን ዘላቂ
ገና ያላደገ ራሱን የማይወክል
ትላንት ቢመጣ ዛሬ የሚሸልል
እኛን አይወክልም የጥንቱ ነን እኛ
የሸሆቹ ፈለግ ሁሌም ነን አንደኛ
የነ ሸህ ዑመር ነን የኮቻው አንበሳ
በዲን ከመጡበት ለነፍሱ ማይሳሳ
መታሰር ክብር ነው እመነኝ ለነሱ
ፊትና መች ቀረና ለዚያ ለንጉሱ
ለአበል ፋጢመቱ ለአለሙ ከውሰር
የኛ መሪወችም ለድል ነው መታሰር
መቼ ይቀርና ሀቅ ይዞ ማሸነፍ
ምልስም አንልም ለገንዘብም ንጥፍ
ይመለስልናል የአህለ ሱኖች መጅልስ
ፍርድ ከአላህ ነው አይቀርም ሳይደርስ
ትላንት የመጣውን አጉል ተክለፍላፊ
ሳይቀጠፍ በፊት እንዳለው ደጋፊ
ተው በሉት ተው በሉት ጌቶቹን ሳንጠራ
ልረከብ የሚለው ያንን ትልቅ ስፍራ
ቅወኛ እኮ አሉበት ያውም ታላቅ ጀግና
የረሱሉ ፈለግ የሆኑትም ዋና
ትሰማኝ እንደሆን ወደነሱ መንገድ
ቀልብህ አይከጅለው እግርህ አይራመድ
የማይነካውን አትንካ ብያለሁ
ሽባ እንደሚያደርጉህ እመነኝ አምናለሁ
ከሳትጋ ጨዋታ አመድ ነው ማቆምያው
አመድ ሳትሆን በፊት ቦታህን እወቀው


by @Seadiii