Get Mystery Box with random crypto!

#ይሄ_ላንተ_እንጂ_ለሱ_ይቺ_ነች ብዙ ትልቅ የሚባሉ በሰዉ አይምሮም ከብደዉ የሚታዩ ነገሮች ብ | Apostolic Grace 💎

#ይሄ_ላንተ_እንጂ_ለሱ_ይቺ_ነች

ብዙ ትልቅ የሚባሉ በሰዉ አይምሮም ከብደዉ የሚታዩ ነገሮች ብዙ ይኖራሉ የሚገርመዉ የእነርሱ መኖር ሳይሆን እነርሱ ቀላል እንደሆኑ የምታይበት አይን መኖሩ ነዉ።
ተራራ ትልቅ ቢመስል ላንተ ነዉ በጣም አስፈሪ የሚመስል ቢኖር እርሱም ላንተ ነዉ።

ትልቁ ችግር ነገሩን በእኛ አይን ማየታችን ነዉ ነገሩን ትልቅ ያደረገብን ልታይ የሚገባዉ በእግዚአብሔር አይን ነዉ።
ብዙ ባንተ ጉልበት ባንተ ገንዘብ ባንተ ብቃት መድረስ የማትችልባቸዉን ነገሮች ባንተ እንደሚያደርግ ከነገረህ ነገሩ ትልቅ ነዉ ከማለት ወጥተህ ነገሩን እግዚአብሔር በሚያይበት አይን እየዉ።
ከቤተሰብህ የመጀመርያዉ ቢልየነር ትሆናለህ ብሎሃል ስለዚህ እርሱ አንተን ባየበት እይታ አንተ ራስህን ማየት ጀምር ።
ከቤተሰብህ የመጀመርያዉ የተቀባህ ሰዉ ትሆናለህ ብሎሃል ስለዚህ ያንን ባንተ አይን ማየት ተዉ እርሱ ባየህ በዚያዉ እይታ ተመልከት።
በመሰረቱ እግዚአብሔር አንተ ነግረኸዉ የሚያዉቀዉ ያንተ ድካም አንተ ነግረኸዉ የሚያዉቀዉ ስንፍናም ሆነ ጥንካሬ የለም።
ነገሮች ሁሉ እንዴት ይቻላል ?? እንዴት ይደረስበታል ?? እንዴት ይሆናል ?? የምትለዉ ለነገሩህ ያለህ ምልከታ ካንተ አንፃር ስለሆነ ነዉ።
አሁን አንድ ምክር ልምከርህ ነገሩን በሙሉ ከእግዚአብሔር አንፃር እየዉ በእርሱ አይን ተመልከተዉ ያን ጊዜ ይህን ዝማሬ ብቻ ስትዘምር ነወለ የምትገኘዉ...

#ኸረ_ላምላኬ_ይቺ_ምንድናት
#በጣም_ቀላል_ናት
#በጣም_ቀላል*2
#ኸረ_ለእግዚአብሔር_ይቺ_ምንድናቴ
#በጣም_ቀላል_ናት
#በጣም_ቀላል*2
ቀላል ነዉ ቀላን ነዉ ቀላል ነዉ *3


@apostolicAnointingElijah
@apostolicAnointingElijah