Get Mystery Box with random crypto!

ከጎንህ ሁሌም እርሱ ብቻ ወዳጄ እስኪ አንድ ነገር አስተዉል ትላንት በዙሪያህ አለን አለን | Apostolic Grace 💎

ከጎንህ ሁሌም እርሱ ብቻ

ወዳጄ እስኪ አንድ ነገር አስተዉል ትላንት በዙሪያህ አለን አለን ሲሉህ የነበሩ ዛሬ አይን ላፈር ያሉህ ትላንት ፍቅራቸዉ ትልቅ የነበረ ዛሬ ላይ የሌለ ትላንት የእግዚአብሔር ሰዉ በርታ ሲሉህ የነበሩ የሆነ ስህተት ሲያዩ ብዬ ነበር እኮ መጀመርያም አላማረኝም ነበረ ያሉ በመንገድ እየተንጠባጠቡ መንገድ የቀሩ ስንቶች ናቸዉ ???

ቆይ እስኪ እንደ ሁኔታዉ የማይልህ በምትሄድበት ጎዳና ሁሉ ከአንተ ጋር የሆነ ይሄዳል ይቀየርብኛል ይተወኛል ይለወጥብኛል ብለህ የማትሰጋበት እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነዉ ዘና ብለህ ተሰማራ በእርሱ እርፍ በል ወዳጄ
“ #እኔ_እግዚአብሔር_አልለወጥም፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም።”
— ሚልክያስ 3፥6

ይህን ብቻ አስተዉል ሁሌም በድካም በብርታት በመዉደቅ መነሳት በመዉጣት በመዉረድ ካንተ ጋራ ያለ ደግሞም የሚኖር እርሱ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነዉ።

ደግሞም እንዲህ ብሎ ቃል ገብቶልናል....

......እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
— ማቴዎስ 28፥19-20
ሰዎች ተነሱብህ ?? እርሱ ካንተ ጋር ነዉ። የከበቡህ ተበተኑ ?? እርሱ ካንተ ጋር ነዉ።
ብቻ እርሱ ካንተ ጋር ይሁን እንጂ የማይገዛልህ የማይታዘዝልህ አይኖርምና ከሰዎች ላይ አይንህን አንሳ ትኩረትህን በአባትህ ላይ አድርግ ትሻገራለህ ትወርሳለህ ትከናወናለህ ድል ትነሳለህ ።

@apostolicAnointingElijah
@apostolicAnointingElijah