2021-09-13 19:20:50
ብርሃን እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ቃል ይሰጣል፤ ሁልጊዜ ቃሉን ሲሰጥ ለመቀበል መዘጋጀት የእኛ ሀላፊነት ነው። እግዚአብሔር ቃሉን ሲሰጥ በልባችን ላይ ብርሃን ያበራል።
“ብርሃንም በጨለማ ያበራል፤ ጨለማውም አላሸነፈውም።”
— ዮሐንስ 1፥5 (አዲሱ መ.ት)
ብርሃን ማለት ምን ማለት ነው?
በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብርሃን ማለት የመለየት፣ የቅድስና፣ የርኀራሄ፣ የችሎታ፣ የእውቀት፣ የመቻል፣ የጥበብ፣ የብልሃተኝነት፣ የፀጋ፣ የምህረት፣ የደግነት፣ የባለሟልነት፣ የውበት፣ ሞገስና ተስፋ ማለት ነው።
Light is commonly a symbol of life.
ብርሃን በጨለማ ላይ ሲበራ ጨለማ ብርሃንን መያዝ ማስቆም ወይም ኃይሉን መቋቋም አይችልም።
የብርሃን አስፈላጊነት ◇ ብርሃን መገለጥን ይሰጣል። ብርሃን ነገሮችን ግልፅ ያደርጋል፣ በሚገባ ያሳያል፣ እንዲገኙ ያደርጋል፣ ትክክለኛ ውሳኔ እንድንሰጥ ያደርጋል። (መዝ 119:130)
Light is for illumination ያብራራል በሚገባ ያብራራል።
◇ ብርሃን መሪነትን ይሰጣል [Light gives leadership]
(ዳን 12:3)
◇ ብርሃን ስልጣንን ይሰጣል [Light gives empowerment]
(ቆላ 1:29)
◇ ብርሃን ለምልክት እና ለዘመናት ነው።
(ዘፍ 1:14፣ ኢሳ 8:18)
በመጨረሻም የብርሃን ምልክትነቱ ከፀሀይ እና ከጨረቃ በላይ የሆነ ነው፤ ብርሃን እግዚአብሔር ሲወክል፣ ጨለማ ደግሞ ሰይጣንን ይወክላል!
መልካም የብርሃን አመት!
ሬቨ. ተዘራ
https://t.me/APOSTLICRIVIVAL
733 viewsⓐ ⓘ, 16:20