Get Mystery Box with random crypto!

አኑ _ poems

የቴሌግራም ቻናል አርማ anu_poems — አኑ _ poems
የቴሌግራም ቻናል አርማ anu_poems — አኑ _ poems
የሰርጥ አድራሻ: @anu_poems
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 378
የሰርጥ መግለጫ

ግጥም ማንበብ ትፈልጋለህ/ትፈልጊያለሽ ??🤔
እዚች ጋር 👉 @anu_poems ተጭነው ጆይን በማለት ብዙ ግጥሞችና ድረሰቶችን ማንበብ ትረካወችንም ማዳመጥ ይችላሉ።
ለሀሳብ አስተያየት @anu_yesua
@anu_poems
@anu_poems
@anu_poems

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-24 21:58:05 [ ቻው ]

... ከተቀመጥንበት ቦታ ላይ ተነስቼ ትቻት ሄድኩ። ቆንጆ ውሸታም ነበረች!! ውሸቷ ስለሰለቸኝ እሷን ማፋጠጥ አቁሜያለሁ.. እንደፈለገች። ምን ገዶኝ?? ሁሉን እያወቅኩ እንዳላወቀ ሆንኩላት..የግንባሯ ደም ስሮች አፍጥጠው እስኪወጡ ድረስ አልሟገትም..አውቅባታለሁ!! የጠየቅኳትን ስትመልስ ካቀረቀረች ዋሽታኛለች። እሷ ግን አልገባትም! ohh sorry እኔ ነኝ የተሳሳትኩት እላታለሁ.. ታምነኛለች። ምክንያቱም የምትፈልገው እሷ እንዳልዋሸች ማወቁን ነው... ዛሬ ግን ትቻት ሄድኩ ስለደከመኝ!!

[የመጀመርያ ቀን]

ከኔ ጋር ሆና እናቷ ደወለችላት.. ላይብረሪ ነኝ ብላ እናቷን ዋሸች። ገና ያኔ መዋሸት እንደለመደች ገባኝ!! ብትነግሪያት ምን ችግር አለው? ብዬ ጠየቅኳት .. ስላልጠበቀች ለሰከከንዶች ዝም አለችኝ ትንሽ አስባ..አቀረቀረች። እንርሳው ብዬ ጨዋታ ቀየርኩ.! በመጀመርያ ቀናችን እኔ የማውቀውን ለእናቷ ዋሸቻት። መዝግቤ አለፍኹ..ቆንጆ ስለሆነች ቶሎ መቁረጥ አልፈለግኩም

[ ተሳሳምን ]

ከንፈሬን ተስሜ አላውቅም አለችኝ..አይኔን እያየች! ስስማት አልፈራችም ፣ ከንፈሮቿ አልተንቀጠቀጡም፣ አይኗን ለመክደን ሰከንዶችን ዘግይታለች ፣ ትንፋሿ አልፈጠነም እንደተረጋጋች ነው ፣ የልብ ምቷ አልጨመረም። ግን ተስሜ አላውቅም አለች። ይሁንልሽ ብዬ ገብቶት እንዳልገባሁ አለፍኩ.. ጣፍጣኛለች እርግጥም። ጣፋጭ ዋሾ ብዬ መዘገብኩላት!

[ ሙዚቃ እያዳመጥኩ ነበር ]

አታላይ ነች ያቺ ልጅ አታላይ ነች
መስላ ገብታ ከሆዴ ቤቷን ሰራች
ላታዛልቅ ላታዋጣኝ ጥላኝ ጠፋች"
ሙዚቃውን አጥፍቼ መፅሀፍ ማንበብ ጀመርኩ። መፅሀፉ የአንድ ሰውን ግለ ታሪክ ያዘለ ነበረ.. አሁን ላለበት ህይወት ያለፋቸውን ውጣ ውረዶች እያጋነነ ያጫውታል.. በህይወቱ ላይ ትልቁ ችግሮቹ ሴቶች እንደነበሩ ገፅ 90 ላይ ይገልፃል " ይመጣሉ ከዛ የተሻለ ሲያገኙ ጥለውኝ ይሄዳሉ። የተሻለ የሚሉት እነሱን በማሽሞንሞን በመጋበዝ በማልበስ የሚፈልጉትን ሁሉ በመስጠት ያለ ተቃውሞ የነሱ ተገዢ የሚሆነውን ሲያገኙ ነው" ይላል.. ገፅ 140 ላይ ደግሞ" እነዛ ጥለውኝ የሄዱ ሴቶችን ለማግኘት ስል ግድ የለሽና ሀብታም ለመሆን ተነሳሳሁ " ይላል.. መነሻውም መድረሻውም ሴት ነች። ስለዚህ ከኔ የጎደላት ምንድነው ብዬ ጠየቅኩ!! ሁሉ ነገሯን እንዳልሽ እያልኩ ማለፌን ነው የማውቀው.. ግን ትታኝ ጠፍታለች።

[ ጥፋተኛ ነበርኩ ]

ራሴን ከሰዎች ሸሽጌ በሲጋራ ሱስ ውስጥ ተጠመድኩ። ሰውነቴ እየተመናመነ መጣ : ፂሜና ፀጉሬ ተንጨባረሩ : የድሮ ሰዓሊ መስያለሁ። የተለመደው ጭር ያለ ቦታ ሄጄ ሲጋራዬን ለኩሼ በሀሳብ እንሳፈፍ ጀመር! የመጀመርያና የመጨረሻ ውሸቷ መሀል የነበረውን አይኗን አስታወስኩ በሁለቱም አጋጣሚ ቀልተው ነበረ.. የመጀመርያው ላይ ውሸቷን መገሰፅ እችል ነበረ። ምን ገዶኝ ማለቴ የመጨረሻ ቀናችን ላይም አይኗ እንዲቀላ ምክንያት መሆኔ ተገለፀልኝ። ማረም የምችለውን ችላ ማለቴ እሷንም እኔንም አጠፋን። የመፅሀፉን ባለ ታሪክ ረገምኩ። ሰዎች እውነተኛውን እንጂ የሚፈልጉትን መንገድ ብቻ እንዲጓዙ መፍቀድ መጨረሻው ተያይዞ መባከን መሆኑን ለምን እንዳልነገረኝ አንገቱን አንቄ መጠየቅ አማረኝ!! ያን ማድረግ ግን አልቻለኩም።

@anu_yesua

@anu_poems
93 views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 09:09:09 ስንት ቀን ጠበቅኩሽ?
( አኑ)

ከመምጣትሽ በፊት ፣ ከመሄድሽ 'ኋላ
የነበረው ጊዜ ቢደመር ቢሰላ
አንድ ቀን ይሞላል?!
አንድ ምሽት አልፏል?!
ፀሀይስ ጠልቃለች?
ጨረቃስ ወጥታለች?

በፍፁም።

ሁሉም እዛው ናቸው
ሲመሽም ሲነጋም ዋጋ የሌላቸው!

"እንዴት?" አልሽኝ አይደል?

አሁን...
ከሰዓታት በፊት
የነበረኝ እምነት የነበረኝ ተስፋ
ከልቤ ሳይጠፋ
መርቀዝ ላይ እንዳለች እንደበራች ሻማ
ንፋስ እያሾራት
ወዲህ ወዲያ እያለች ከአየሩ ጋራ እንደምትሻማ!
እንዲያ ሆና ልቤ
እስክትመጪ ድረስ የጠበቅኩሽ ሁሉ
የሆንኩልሽ ሁሉ
የናፈቅኩሽ ሁሉ
ስትመጪ ጊዜ በዜሮ ይጣፋሉ!
ምንም ይሆናሉ!!

እልፍ ዘመናትን ቆሜ ስጠብቅሽ
ምንም እንዳይመስልሽ!
ያገኘሁሽ ለታ
አይንሽን ያየሁ ቀን
ዜሮ ነው ስቃዬ
ደስታዬ ሲደቀን!

0 ቀን ጠበቅኩሽ።

@anu_yesua
@anu_poems
116 views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 22:51:55 ነገ ጠዋት 12:30 ላይ በብስራት fm የመንጌ ውሽሚት ከሚለው መፅሀፍ ላይ ትረካዬን እንድታዳምጡ እጋብዛለሁ።

አቶ አኑ.... ከማይታይ ፊርማ ጋር
217 views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 19:31:24 ሰላም ለናንተ የአኑ poems አባላቶች ትረካዎች ይቀጥሉ ወይስ በግጥሞቻችን ብቻ እንዝለቅ?

አስተያየታችሁን @anu_yesua ላይ ያድርሱኝ
213 views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 09:36:22 ሞገደኛው ነውጤ....የመጨረሻው ክፍል 5

ደራሲ... አበራ ለማ
ተራኪ... አንዋር ሚፍታ
221 views06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 22:02:50 ሞገደኛው ነውጤ... ክፍል 4

ደራሲ... አበራ ለማ
ተራኪ... አንዋር ሚፍታ
200 views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 14:47:15 ሞገደኛው ነውጤ.... ክፍል 3

ደራሲ... አበራ ለማ
ተራኪ... አንዋር ሚፍታ
197 views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 21:19:06 ሞገደኛው ነውጤ.. ክፍል 2

ደራሲ.. አበራ ለማ
ተራኪ.. አንዋር ሚፍታ

ለአስተያየት... @anu_yesua
188 viewsedited  18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 09:41:53 ሞገደኛው ነውጤ.. ክፍል 1


ደራሲ.. አበራ ለማ
ተራኪ.. አንዋር ሚፍታ

ለአስተያየት @anu_yesua
186 viewsedited  06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ