Get Mystery Box with random crypto!

የደራሲው ባዮግራፊ አንተነህ ጌታቸው በመስከረም 1/1991 ዓ.ም ከአዲስ አበባ 85 ኪ.ሜ ርቀት | ሳይንስኛ™

የደራሲው ባዮግራፊ

አንተነህ ጌታቸው በመስከረም 1/1991 ዓ.ም ከአዲስ አበባ 85 ኪ.ሜ ርቀት በምትገኘዋ ጉራጌ ዞን ጥያ ከተማ ተወለደ፡፡ የበጥያ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርን የተከታተለ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪውን በፊዚክስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 4ኪሎ ግቢ በ2013 ዓ.ም በማዕረግ ጨርሷል፡፡

ከአስር በላይ የምርምር ስራዎች ያሉት ሲሆን በተለይም ዘመናዊ ኦርጋኒክ ማዳበሪያ የፈጠራ ስራው ለኢትዮጵያ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ አንተነህ ለስነጽሑፍ ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት ያለው ሲሆን አራት መጽፍቶችን ያዘጋጀ ሲሆን ይህ ‹‹ማወቅ›› የሚለው መፅሐፉ በተለይም ሰዎች ለሚያነሷቸው የተለያዬ ጥያቄዎች ለምሳሌ ቴክኖሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባይሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ፣ ህብረተሰብ፣ ስፖርት እና ጂኦግራፍ እነዚህን መሠረት አድርጎ ጥያቄዎች ያነሳል፤ እንዲሁም መልሶቹንም በደንብ አብራርቶ ይመልሳል።



የደራሲው አስተያየት

ይህ መፅሐፍ እንዳዘጋጅ ያነሳሳኝ ዋናው ምክንያት ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች እና ብዙ ሰዎች የሚጠይቁትን ጥያቄዎች የሚያብራራ መፅሐፍ እንድፅፍ አነሳስቶኛል፤ ስለዚህም የብዙዎቻችን ጥያቄ የሚመልስ እና አዲስ ነገሮች የምናውቅበት መፅሐፍ ነው። መፅሐፉ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ቴክኖሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባይሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ፣ ህብረተሰብ፣ ስፖርት እና ጂኦግራፍ እነዚህን መሠረት አድርጎ ጥያቄዎች ያነሳል፤ እንዲሁም መልሶቹንም በደንብ አብራርቶ ይመልሳል።

ማወቅ አዲስ ነገርን እንድንፈጥር ያነሳሳናል። ስናውቅ ነገሮች በቀላሉ መረዳት እንችላለን። እንዲሁም ስናውቅ እናሸንፋለን። ለምሳሌ፡ "የቴኒስ ጨዋታ ማሸነፍ ብትፈልግ ግዴታ የቴኒስ እግጋት ማወቅ ይጠበቅባል!" ለዚህ ነው ማወቅ የተግባሮች ሁሉ መነሻ የሆነው። ይህ የሁሉም ሰው ጥያቄ ይመልሳል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። መፅሐፉ ገዝታችሁ የማይገዛውን እውቀት ያግኙ/ ይገብዩ። እውቀት ዘላለማዊ ነው። የአወቁትም ማሳወቅ የማወቅ ጥበብ ነው። በሁሉም ሰው እድሜ የተዘጋጀ መፅሐፍ ነው።

•••

"ማወቅ እና የእውቀት መንገድ" በአንተነህ ጌታቸው
በቅርብ ቀን…
ይሸመት…
ይነበብ…