Get Mystery Box with random crypto!

#የእውነትንመንገድ ከደገና #ዓይኖቻችንን ከፍቶ እንዲያሳየንና እንዲመራን #ወደ እርሱ እንጩህ ዮሐ | 🌎እቅብአት

#የእውነትንመንገድ ከደገና #ዓይኖቻችንን ከፍቶ እንዲያሳየንና እንዲመራን #ወደ እርሱ እንጩህ
ዮሐንስ ወንጌል 16
13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
14 እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና።
15 ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ፡— ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ።

ወዳጆቼ #ወደእውነትመንገድ የሚወስደው #የእግዚአብሔርመንፈስ ብቻ ነው። በሰለጠኑ ሀገሮች #ከእግዚአብሔርመንፈስ ጋር የሚሄዱ #ሰዎች በሰለጠኑት ሀገር ሲጠሩት #Revival ይሉታል፤ በኛ ደግሞ የእውነት መንገድ ተከታዮች እንለዋለን:: ታዲያ የእውነት መንገድ ተከታዮች መባሉ የሚለው ይቅርና እኛ የእውነት መንገድን ተከትለናል፥ የእውነት መንገድ መከተል ክርስቶስን አንድ ጊዜ ብቻ በማስገባት አይገኝም...#ሁልጊዜ በማስገባት ነው እንጂ...
#ታዲያ አሁን የእውነት መንገድ ላይ ነን...?
የእውነት መንገድ ላይ ያለ አይዋሽም::
የእውነት መንገድ ላይ ያለ አይሰርቅም::
የእውነት መንገድ ላይ ያለ በወንድሙ ላይ አይተናኮልም::
የእውነት መንገድ ላይ ያለ ወንድሙን አይገፋም::
የእውነት መንገድ ላይ ያለ በወንድሙ ክፉ ነገር ላይ አይመኝም::
የእውነት መንገድ ላይ ያለ አይታበይም::
የእውነት መንገድ ላይ ያለ ወንድሙን አያማም::
የእውነት መንገድ ላይ ያለ ለወንድሙ መልካምን ሁሉ ይመኛል
#ወዳጆቼ እንግዲህ #በእውነትመንገድ ላይ ያለ እሄንን መስሎች ነው #መገለጫው... #ታዲያ አሁን የእውነትመንገድ ላይ ነን...? ለሚለው #መልስ አይደለንም::
#የእውነት መንገድ #መለኪያው ፀሎት ማድረግ ስለቻልን አይደለም፤ እንዲያው ሌሎቹም #ፀሎትን ማድረግ ይችላሉ::
#የእውነትመንገድ #መለኪያው #ልሳን #ተሞልተን ስለተናገርን #አይደለም...ሌሎቹም #በጨለማው ዓለም ላይ ያሉ ሰዎች #ልሳን #ተሞልተው የሚናገሩ አሉ::
#የእውነት መንገድ #መለኪያው #ተቀብተን #ህልምና #ራዕይ ማየት ስለቻልን አይደለም...#ሌሎቹም በጠላት #ተቀብተው #ራዕይና #ህልም ያያሉና::

#ወዳጆቼ #የእውነትመንገድ መለኪያው #በእውነት መንገድ ላይ መሄዳችን እንዲሁም መሆናችን ነው:: #ስለዚህ ለሁላችን #ፈውስ ያስፈልገናል፥ ምክንያቱም #የእውነት መንፈስ የሆነው፥ #የመንፈስ በኩር የሆነው #መንፈስቅዱስ ከደገና ስለሚያስፈልገን...#ወተቱን ጠጥተን ሳንጨርስ #ወደስጋ አንሂድ...#ስጋውን በልተን ሳንጨርስ #ወደአጥንቱ አንሂድ...

#የእኛ አምላክ #ምህረቱ እስከ ለዘላለም ናትና...#መንግስቱ በምህረቱ #የፀና ነውና፤ #የእውነትንመንገድ ከደገና #ዓይኖቻችንን ከፍቶ እንዲያሳየንና እንዲመራን #ወደ እርሱ እንጩህ

#Revival....
ተባርካችኃል
#Join & #Share
@anointedbyholyspirit