Get Mystery Box with random crypto!

የዓለማችን ፲ ያልተፈቱ ሚስጥሮች በዙሪያው የሚገኝን ነገር በጥልቀት መመርመር እና ከሚከሰቱ | ግዮን ቲዩብ

የዓለማችን ፲ ያልተፈቱ ሚስጥሮች




በዙሪያው የሚገኝን ነገር በጥልቀት መመርመር እና ከሚከሰቱ ነገሮች ባሻገር ያለውን ምክኒያት ማወቅ የሰብዓዊ ፍጡር ተፈጥሮ ነው፤ነገር ግን አንዳንድ ክስተቶች ተብራርተው አይገለጹም። አንዳንድ ታሪኮች ደግሞ የእያንዳንዱን ሰው ቀልብ መሳብ የሚችሉ በጣም አጐጊ ናቸው።እነዚህ አጉዋጊ ታሪኮችም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሁላችንንም ትኩረት ሊስቡ እና በታሪኩ ላይ ፍላጎት እንዲያድርብን ያደርጋሉ። አፈታሪኮችም የተወሰነ የወሬ ቅመም ታክሎባቸው ይበልጥ አጉዋጊ እንዲሆኑ ይደረጋሉ።ለረጅም ጊዜያት ያህል ሁሉንም ያስደነገጡ እና ቀልብ የሳቡ የዓለማችን 10 ያልተፈቱ ሚስጥሮች አሉ።እነዚህም ...

፩ . ዲ.ቢ ኩፐር

በፖርትላንድ፣ኦሬጋን፣ሲያትል እና ዋሽንግተን መካከል ቦይንግ 27 አውሮፕላንን የጠለፈውና ወዳልታወቀ ስፍራ በፓራሹት የወረደው ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ዲ.ቢ ኩፐር የሚባል ስም ነበረው።ግለሰቡ ላገታቸው ሰዎች ማስለቀቂያም 200,000 ዶላር አግኝቷል።ኤፍቢአይ በጣም ከፍታ ካለው ስፍራ ላይ በመዝለሉ አደጋ ስላለው አይተርፍም ብሎ ቢደመድምም ቢደርስም፣ የመጨረሻ ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ ሃሳብ አሁንም ድረስ አልተገኘም።የግለሰቡ ማንነትም እስካሁን ድረስ ለሁሉም ሚስጥር እንደሆነ ነው።

፪. የታማም ሹድ ጉዳይ

በአውስትራሊያ ሶመርተን ባህር ዳርቻ ላይ በመስከረም 1፣1948 ዓ.ም፣ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሞቶ የተገኘው ማንነቱ ያልታወቀ ሰው የሞቱ ምክኒያት "ካልተፈቱ አብይ ሚስጥራዊ ጉዳዮች አንዱ" ተደርጎ ይቆጠራል።በወቅቱ ያለማቈረጥ እየተካሄደ በነበረው የቀዝቃዛው ጦርነት ምክኒያት መሀከለኛ እድሜ ላይ የሚገኘው ሰው ባልታወቀ መርዝ በመሞቱ፣በልብሱ ላይ የሚገኙ የጽሁፍ
ማስረጃ ምልክቶች በሙሉ በመወገዳቸውና የሆነ ሚስጥራዊ ጽሁፍ የተጻፈበት ቁራጭ ወረቀት በኪሱ ውስጥ በመገኘቱ ማነነቱ ያልታወቀው ሰው ሰላይ የነበረ ተደርጎ እንዲቆጠር አድርጎታል።ይሁን እንጂ ግለሰቡ የደህንነት ሰው ነው ብሎ ያመን አንድም መንግስት ግን አልነበረም።የሰውዬው ማንነት ባለመገኘቱም የጉዳዩ ስም "ታማም ሹድ" ለመሰኘት በቅቷል።ትርጉሙም "አለቀ" ወይም "ተፈጸመ" ማለት ቢሆንም ምርመራው በመቀጠሉ ጉዳዩ አሁንም ድረስ ሚስጥር ነው።

፫.የጠፋችው የአትላንቲስ ከተማ

እስካሁን ድረስ ሚስጥራዊ የሆነ ባህር ውስጥ የሰጠመች ጥንታዊ ከተማ አለች የሚል ሃሳብ አለ።አፈ ታሪክ ነው ወይስ ሚስጥር?ስለዚህች ከተማ በርካታ እሳቤዎች ያሉ ሲሆን አንዳንዶች አህጉር ናት ሲሉ፣አንዳንዶች ደግሞ ጉዳዩን ከተማነቷን እውነተኛ አድርገው ይቆጥሩታል፣ሌሎች ግን የውሸት ታሪክ ነው ይላሉ።ስለጠፋው ስልጣኔ የጻፈ የመጀሪያ ሰው ፕሌቶ ሲሆን እንደሱ መረጃ መሰረት አትላንቲስ የአቴንስ ባላንጣ ከተማ ነበረች በዚህም የተነሳ ከአማልክቶች ቅጣት ደረሰባት።የጠፋቸው አትላንቲስ ከተማ ቤርሙዳ ላይ የጠፋች መርከብ ተደርጋም ትታሰባለች።(ባሀፈው የገለፅነው አቋም እንዳለ ሆኖ)

፬. የቮይኒች ያለታተመ ረቂቅ መጽኃ

መፅሃፉ ስያሜውን ያገኘው እንግዳ የሆኑ የተለያዩ ምስሎችን፣ ክስተቶችን እና የትኛውንም የተክል ዘር የማይመስሉ አትክልቶችን የያዘ ፍፁም በማይታወቅ ቁዋንቁዋ የተጻፈ 240 ገጽ ያለውን መጽሃፍ ካስተዋወቀ ፖላንድ-አሜሪካዊ ከሆነው ኤም.ቮይኒች ከተሰኘ የመጻህፍ ነጋዴ ነው።በገፆቹ መካከል የተገኘ ንጠረ ነገር እንደዳመለከተው መጽሃፉ የተጻፈው ከ1024-1438 ዓ.ም መካከል ነው።የመፃህፉ ፀሃፊም እስካሁን አይታወቅም። በመፃህፉ ውስጥ የሚገኙ ምስሎች የተወሰኑ ስነጠፈር ነገሮችን የሚያመለክቱ በመሆናቸውም መፅሃፉ "የዓለማችን ዋነኛው ያልታተመ ረቂቅ መፅሀፍ" ለመሰኘት በቅቷል።

፭. የዋው! ምልክት

በ1977 በአንድ ሞቃታማ ምሽት ከዳላዋሬ፣ኦሃዮ አቅራቢያ የሰውን ልጅ ታሪክ ለአጭር ጊዜያት ያህል እንደሚቀየር ያመላከተ ምልክት በአንድ ትልቅ ቴሌስኮፕ አማካኝነት መያዝ ተቻለ። መልክቱ ከሌላ አለም የተላከ እና ለሰባ ሰከንዶች ያህል የቆየም ነበር።ምልክቱም ቃላትና ቁጠሮች የሚቀያየሩበት ነበር።በምልክቱም ላይ በክብ ቅርፅ ውስጥ "ዋው" የሚል ጽሁፍ ተፅፎበት ነበር። በዚህም የተነሳ "ዋው" ምልክት ለመሰኘት በቅቷል። በርካታ ባለሙያዎች እና የስነጠፈር ተመራማሪዎች የምልክቱን ትክክለኛ ምንነት ለመረዳት ሙከራ አድርገው የነበር ቢሆንም፣ አልተሳካላቸውም፤ምልክቱም ከዚያ በኁዋላ ፍጹም በድጋሚ አልተገኘም።

፮. የታኦስ ሰቅጣጭ ድምጽ

በ1950 ዎቹ አንዳች የጥዝታ እና የሚርገበገብ ድምፅ በሜክሲኮ ከተማ ነዋሪዎች ተሰማ። በአከባቢው 4,700 የሚደርሱ በርካታ ሰዎች የሚኖርበት ሲሆን ድምጹን የሰሙት በርካቶችም ድመጹ የከባድ መኪና ሞተር ድምጽ የነበረው መሆኑን ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን ሚስጥራዊው ድምፅ የሚረብሽና የሚሰቀጥጥ ስለነበርም ሰዎችን ረፍት በመንሳትና በመረበሽ ነስር ለመፍጠርም ምክኒያት ሆኖ ነበር።በርካታ ሳይንቲስቶችና መርማሪዎች ይህን ጉዳይ በመመርመር ላይ ተሳታፊ የነበሩ ቢሆንም ትክክለኛ ምክኒያቱን ግን ሊደርሱበት አልተቻላቸውም።

፯. የሎች ነስ አስፈሪ ፍጡር(ግዙፍ ጭራቅ)

በዚህ ዘመናዊ ዘመን አስፈሪ ጭራቅ አለ ብሎ ማመን አስቸጋሪ ነው!የሎች ነስ አስፈሪ ፍጡር ግን ያልተፈታ ሚስጥር ሲሆን በርካታ ሰዎችም ይህን ግዙፍ አስፈሪ ፍጡር ተመልክተውታል፣ነገር ግን ያ ፍጡር አሁንም ድረስ ሚስጥር እና ያልተፈታ ጉዳይ ነው።የዳይኖሰር ቅርፅ ያለው ይህ አስፈሪ ፍጡር ሎች ነስ በተሰኘው የስኮትላንድ ጥልቅ ኃይቅ ውስጥ ተደብቆ ነበር ተብሎ ታምኗል።በርካታ ፎቶግራፎች እና የድምጽ ስካኖች የአውሬውን አካላዊ ሁኔታ ቢያሳዩም መረጃዎቹ ሙሉ በሙሉ አመኔታ ያማይጣልባቸውና በጥርጣሬ የተሞሉ ነበሩ።ከ1930 ዓም አንስቶም አሉባልታዎች በከፍተኛ ሁኔታ ቢኖሩም ሚስጥሩ ግን አሁንም ድረስ መነጋገሪያ ነው።

፰. አመሊያ ኢርሃርት

አመሊያ ኢርሃርት አትላንቲክ እና ፓስፊክ ውቅያኖስን ለብቻዋ ያቁዋረጠች የመጀመሪያዋ ሴት የተሰኘች የበርካታ ባለሪከርድ አሜሪካዊት ፓይለት እና ፀሃፊ ናት።ነገር ግን በሃምሌ 2፣1937 ዓ.ም በረራ ላይ እያለች በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቂያኖስ የሆነ ስፍራ ላይ አውሮፕላኗ ድንገት ይሰወራል።በዚያው ድንገተኛ አጋጣሚም ዝናዋና ስሟ እንዲሁም ህይወቷ ለመጥፋት ችሏል።የመጥፋቷ ጉዳይ ሚስጥርም አሁንም ድረስ አልተፈታም።እንደእንግሊዝ አርኪዎሎጊስቶች መረጃ መሰረት በ1999 ዓ.ም በፓስፊክ ደሴት ላይ የኢርሃርት ዘረመልን የያዘ የተከሰከሰ አውሮፕላን ያገኙ ቢሆንም፣መረጃው ያልተቁዋጨ በመሆኑ ሚስጥሩ እንደቀጠለ ነው።

፱.ሞገደኛው ጃክ


በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ አከባቢ የቆዳ ባለኮፍያ ካባ የሚለብስ (ያለ ጥርጥር ነውጠኛ ነፈሰ ገዳይ የሆነ)በለንደን ነዋሪዎች ላይ ፍራቻና ሽብርን አንሰራፍቶ ነበር።ገዳዩ ሰዎችን የሚገድለው ያለርህራሄና እና ለበርካታ ጊዜያት ያህል በማጥቃት ነበር።በዚህ ጉዳይ ላይ ዓመታትን ያሳለፈ ትሬቨር ማሪዮት የተሰኘ አንድ ጡረታ የወጣ የፖሊስ መርማሪእንደተናገረው "ምናልባትም ይህ ጉዳይ በእንግሊዝ ታሪክ ታላቁ ያልተፈታ ሚስጥራዊ የወንጀል ታሪክ ነው።" ብሏል።
እና አስረኛውና የመጨረሻው ከዚ በፊት የተወያየንበት ቤርሙዳ ትርያንግል ነው።
ከዜና እንቶ የተገኘ



ይህን ቻናል ለመቀላቀል

https://t.me/ANDROMEDAMT