ኃጢአትን ለንስሓ አባት/ለካህን መናዘዝ/ @And_Haymanot ተወዳጆች የተሀድሶ መናፍቃን ምዕመናንን ከንስሃ ህይወት ለማራቅ ሃጢአትን ለንስሃ አባት መናዘዝ አያሥፈልግም በማለት ሀጢአትን ለካህን መናዘዝን ይቃወማሉ፡፡ እናት ቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታሥተምራለች @And_Haymanot ካህን የእግዚአብሔር ምሥጢራት አስፈፃሚ ስለሆነ ኃጢአትህን ንገረው ። ይህን ቅዱስ ጳውሎስም አስረግጦ ጽፎልሃል ። " እንዲሁ ሰው እኛን እንደ እግዚአብሔር ምሥጢር መጋቢዎች ይቁጠር ።" 1ቆሮ 4*1 አስቀድሞም በነቢዩ ሚኪያስ ያደረው እግዚአብሔር ሲናገር "ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነው "ይላል ። ኃጢአትህን ለካህን በምትነግርበት ጊዜ የሚሰማህን ኃፍረት መሸማቀቅ ሁሉ ችለህ የመመለስን ምሥጢር እንዲያስፈጽምልህ ስትጥር እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ድርጊትህን እንደ ታላቅ መሥዋእትነት ቆጥሮልህ ኃጢአትህን ሁሉ ይደመስስልሃል ።/ ዩሐ 20*21*23/ ማቴ 18*18 ካህኑ ክርስቶስ በሰጠው በዚህ ሥልጣን መሠረት ከኃጢአት እሥራት መፈታትህን ያረጋግጥልሀል ። ሕይወት ለሚሆነው ሥጋና ደሙ እንድትበቃም ያደርግሃል ።/1ቆሮ 11*27/ በሕይወትህ ውስጥ የሚታዩትን ጉድለቶች (መንፈሳዊ ድክመቶች )እየተመለከተም እንዴት አሸናፊ መሆን እንደምትችል የሚመክርህ መንፈሳዊ መሪህ ካህን የንስሓ አባት መሆኑንም አትዘንጋ ። ለካህን ኃጢአትን መናዘዝህ በራሱ የሚያተርፍልህ ነገር አለው ። ኃጢአትን መልሰህ ስትናገረው ለአንተ ለራስህ ምን ያህል አሳፋሪ እንደሆነ ይሰማሃል ። ይህም ዳግም እንዳትመለስበት ታላቅ ትምህርት ይሰጥሀል ። መጽሐፍ ቅዱስም የሚለው ይህንኑ ነው ። " እርስ በእርሳችሁ ኃጢአታችሁን ተናዘዙ ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ሰው ስለሌለው ይጸልይ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች ።" /ያዕ 5*16 / ምንጭ @pope_shenouda @pope_shenouda ___፩ ሃይማኖት_______ ላልደረሳቸው እናዳርስ @And_Haymanot ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተክርስቲያን @And_Haymanot #______አትታደስም______! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር) @And_Haymanot ኦርቶዶክስ መልስ አላት @And_Haymanot ============================ ፩ ጌታ ፩ ሃይማኖት ፩ ጥምቀት ኤፌ4:5 2.7K views16:11