Get Mystery Box with random crypto!

​​ገድሉ ተአምራቱ @And_Haymanot ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው  ጣኦትን አዋርዶ የተሸ | ፩ ሃይማኖት

​​ገድሉ ተአምራቱ

@And_Haymanot

ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው 
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው 
የተዋሕዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ 
አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ 
አዝ ------------------ 
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፈር የታጠቀ 
ንጹሕ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ 
የጸጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ 
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ 
አዝ --------------------- 
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት 
ባላስድስት ክንፉ ጻድቁ የእኔ አባት 
እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ 
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ 
አዝ ----------- 
ከካህናት መካከል ኅሩይ ነው አቡዬ 
መጣው ከገዳምህ ልሳለለምህ ብዬ 
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት 
ወልድ ዋሕድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት 
አዝ ----------------- 
የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት 
ጥላህ ያረፈበት ሆንዋል ጸበል እምነት 
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ 
ይሰብካል ተክለአብ ዛሬም እንደጥንቱ 
አዝ ------------------
@And_Haymanot
@And_Haymanot