Get Mystery Box with random crypto!

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገት አስመልክቶ በጥያቄና መልስ የቀረበ ጽሑፍ ነው። እናን | ፩ ሃይማኖት

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገት አስመልክቶ በጥያቄና መልስ የቀረበ ጽሑፍ ነው። እናንተም ተጋበዙልኝ።

ጥያቄ ፩፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ድንግል ማርያም ዕርገት አይናገርም። ታድያ "ዐረገች" ማለታችሁ ስህተት አይኾንም?

መልስ ፩፦ አንድ ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስላልተጻፈ ብቻ "ሀሰት" ሊባል አይችልም። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የአምስት ሺሕ ዓመታትን ታሪክ የያዘ እንደ መኾኑ ኹሉንም ታሪኮች በአንድነት ጠቅልሎ ይይዛል ማለት ዘበት ነው። የአንድ ንጉሥ ታሪክ እንኳን እጅግ በጣም ብዙ ገጽ መጽሐፍ ሊወጣው እንደሚችል እናውቃለን። ታድያ "በግልጽ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስላልተጻፈ ሀሰት ነው" ልንል የምንችለው እንዴት ነው?

አንድም በመጽሐፍ ቅዱስ መገደብ አንችልም። ምክንያቱም "መጽሐፍ ቅዱስ እንደ እገሌ ከሰማይ ወረደ" ብለን አናምንም። መጻሕፍቱ በአበው፣ በነቢያትና በሐዋርያት እጅ በተለያየ ጊዜና በተለያየ ቦታ መጻፋቸውን እናውቃለን። ከእነዚህ ውጪም በሐዋርያቱ ስም የተጻፉ የሀሰት መጻሕፍትም ነበሩ። እነዚህን እውነተኛዎቹንና ሀሰተኛዎቹን መጻሕፍት ከዓለም ያሰባሰቡትና የለዩት አባቶች ናቸው። ለመጻሕፍቱም ቅድስና የሰጡት እነርሱ ናቸው።

በመኾኑም መጽሐፍ ቅዱስን ለማመን የአባቶችን አማናዊነት መቀበል ግድ ይለናል። ካልኾነ ግን እነርሱ የራሳቸውን አስተምህሮ ተከትለው እውቅና የሰጧቸው ቅዱሳት መጻሕፍት በጠቅላላ ጥርጣሬ ውስጥ ይገባሉ። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምን ኹሉ በእመቤታችን ዕርገት ማመን ይጠበቅበታል። ምክንያቱም ለመጻሕፍቱ ቅድስና እውቅና የሰጡ አባቶች በጠቅላላ በእመቤታችን ዕርገት ያምናሉ።

ጥያቄ ፪፦ እውን ድንግል ማርያም ዐርጋ ቢኾን ኑሮ ሐዋርያቱ በግልጽ ያልተናገሩትና በመጽሐፋቸው ላይ ያልጻፉት ለምንድን ነው?
......
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot