Get Mystery Box with random crypto!

እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ???       #Par | የዲነል ኢስላም ነኝ 🌙🌙

እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ???

      #Part

ፀሀፊ #አሚር

     ፍቅር ....ፍቅር ማለት ምን ማለት ነዉ ??? ማንኛችንም ስለፍቅር ስንጠየቅ መልሳችን ሀሳባችንን መግለፅ አንችልም ...ፍቅርን ብዙ ጊዜ ተጠያቂዉ ፍቅርን ግለፅ ሲባል ሊገልፀዉ የማይችል ግዑዝ ነገር ነዉ፡፡ አንድ ሰዉ አፈቅርሻለሁ ወይም አፈቅርሀለሁ የሚባለዉን ድምፅ ከሌላ ሰዉ ሲሰማ ከበፊቱ ካለበት አንድ ደስታ ይጨምራል ...ግን አፈቅርሻለሁ ያለዉ ሰዉ...ፍቅር ምንድን ነዉ ብለህ ስጠይቀዉ እንጃ ስለፍቅር መግለፅ አልችልም ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ለመናገር ቀላል የሆነ ለመግለፅ ግን የከበደ ፍቅር ትርጉሙ ምንድን ነዉ ??? ትርጉም አልባ መልስ ያስተናግዳል፡፡
     ስለፍቅር እናንተ ምን አመለካከት አላችሁ???ፍቅር ማለት ዛሬ ተዋወቁ ነገ ተዋደዱ ከዛ ተጣሉ ..ከዛም አለቀሰ አለቀሰች ታረቁ ..ከዛስ............ይቀጥላል ሆነ ነገሩ፡፡ ፍቅርን በአፍህ መግለፅ ካልቻልክ መግለፅ ያልቻልከዉ ሶስት ፊደላት አሉ እነሱም ፍ...ቅ.....ር አይነቱ ይለያይ እንጂ በማንኛዉም ሰዉ ዉስጥ ያለ ነገር ነዉ ...ነገር ግን የፍቅር አይነቶች የተለያዩ ናቸዉ ፍቅርን በሰዉ ልጅ ብቻ ማመሳሰል አይቻልም፡፡
   ግን .ፍቅር ማለት ምን ማለት ነዉ??? እኔም ትርጉሙ ይጠፋኛል ፡፡ከፍቅር ሁሉ ከባድ ግን የወደዱትን ሰዉ ለራስ እንደማይሆን ለእሱ መስዋአትነት ከፍለን የሌላ እንደመሆን የሚያሳዝን የለም፡፡ ወንድ ልጅ ፍቅሩ ከላይ ነዉ የሚሉ ወገኖች አሉ ..የወንድ ልጅ ፍቅር ግን እስከ ጥግ እንደሚሄድ እና ወንድ ልጅ ባህሪዉ ሴትን የማያምንበት ምክንያት መጀመሪያ በሴት ልጅ ፈተና ተለክፎ ሁኖ ሊሆን ይችላል  .......
    ግን ይሄ ትርጉሙን በአፋችን መግለፅ የማንችለዉ ፍቅር የሚለዉ አንድ መልስ አለዉ መልሱም....የመጀመሪያዉ ፍቅርን ካመጣዉ ..ፍቅር የሚባልን በሰዉ ልጅ ላይ ካስቀመጠዉ ..ከፈጣሪህ ከአላህ ፍቅር ስጀምር...ምንም ፍቅር የሚባል ቢመጣብህ ከፈጣሪህ ፍቅር በላይ እንደማይሆን 100% እርግጠኛ ሁን(ኚ)
     ታሪኬን ከስሜ ልጀመር ከድር መሀመድ አህመድ ይባላል የተወለድኩት ደቡብ ወሎ ሀርቡ ከተማ ነዉ፡፡ ቀጠን ብየ በባህሪም በመልክም ሸጋ የሆንኩ ልጅ ነኝ ... የቤተሰቦቼ አኗኗር በጣም ድሆች ስንሆን ግን በቀዷ እና ቀድር የምናምን በአለን ተብቃቅተን የምናድርD ነን፡፡ የምንኖረው መንግስት በሰጠን በቀበሌ ቤት ነው፡፡ አባቴ ስራ አይሰራም .... እናቴም ብትሆን እድሜዋ ከ 60-70 ይደርሳል፡፡ታላቅም ታናሽም ወንድሞች አሉኝ፡፡
 
ሀርቡ ከተማ ለደሴ ደግሞ የ 20 ብር ትራንስፖርት ሲሆን ርቀቱ 40 ኪ.ሜ ገደማ ነው ወደ ኋላ ስንመላስ የሀፊዞች የጀግኖች ሀገር ከሚሴ ታዋስነናለች ርቀቱ 30 ኪ.ሜ ሲሆን ለአዲስ አበባ ደግሞ 345 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ 
    ሀርቡ የአየሯ ፀባይ ወይና ደጋ ነው ለአኗኗር በጣም ይመቻል ..በተጨማሪም
ሀርቡ የሸንኮራ አገዳ''ወደ አዲስ አበባ ወደ  አፋር ትልካለች፣የቦርከናን ወንዝ በአግባቡ መጠቀም ቢያቅታትም የአትክልት ና የፍራፍሬ ከተማ ናት።
''ሀርቡ ሌላ አንድ የተፈጥሮ ሀብት አለት።በከሀርቡ ከተማ  በግምት 8,ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ፍልዉሀ አላት
ፍሉሀውን የውጭ ሀገር ዜጎች ሳይቀር እየመጡ ህመማቸውን''ይፈወሱበታል፡፡
    እድሚየ ሲደርስ እንደማንኛዉም ተማሪ የተማርኩ ሲሆን፡፡ የትምህርት ቤት ህይወቴ ብዙም ትኩረት የለኝም ነበር  :: .ከ1 እስከ 8 ሀርቡ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ሲሆን 9 እና 10 ደግሞ ሀርቡ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነዉ፡፡
   የአላህ ፈቃድ ሁኖ ወደ ዲን አለም የገባሁት በልጅነቴ ነበር..አባቴ ዲኔን እንድይዝ እንጂ ብዙም ለአካዳሚክ ትምህርት ትኩረት የለዉም ነበር.... ገና የሶስተኛ ክፍል ተማሪ ሁኜ ቁርዐን አክትሚያለሁ፡፡ ከዛም በየደረጃወ ኪታብ እየቀራሁ አደኩኝ፡፡ የፊቂህ ደርስም ቢሆን የሻፊኢን መዝሃብ ሰፊና ሹጃአ ባፈድል እያልኩኝ .... ሶርፍ ጀመሬ ነው የትውኩት .....
    ቁርዐን ተፍሲርም ጓደኛየ ጋር አብሬ ቀርቻለሁ፡፡ ሃዲስ እንቀራለን ኡሱሉ ሰላሳ ,,ኪታቡ ተውሂድ,, አርባ ሃዲስ ,,ቡልገል መራም ,,ሪያዱ ሷሊህ ,,ተጅሪድ ኢብነ ማጅህ እና ቡኻሪና ሙስሊም ቀርተናል
.....ተርቢያ የሚያደርገን ደግሞ የመስጅዳችን ሙአዚን ጀማል ዩሱፍ ይባላል ጎልማሳ ወጣት ነው እሱ ቂርዐት የቀራው ገጠር ተቸግሮ እንደሆነና እኛ ከተማ እየኖርን ትምህርት እየተማርን በትርፍ ጊዜያችን ካልቀራን በአላህ ዘንድ እንደምንጠየቅ ይመክረናል ዳእዋ እንድናደርግ ይጎተጉተናል አረብኛ እንድንጽፍ የዳእዋ ኖት ራሳችን ከኪታብ አውጣተን እንድናዘጋጅ ያስተምረናል ያዘጋጀነውን ያርምልናል::
     ወንበር ላይ ያስቀምጠንና ከፊታችን ድንጋይ ደርድሮ ድንጋዩ ሰው እንደሆነ አስቡት ከዚያ ዳእዋ ማድረግ ጀምሩ ይለናል ብቻ ዳኢወች ሆንን ለመጀመሪያ ጊዜ ዳዕዋ ለማድረግ መስጅድ ስቆም አስታውሳለሁ ከፈጂር ሶላት በኋላ ነበር እጥር ምጥን ያለ ከ 5 ደቂቃ አትበልጥም ግን የመጀመሪያየ ሆኖም እየፈራሁ ያደረኩት ዳእዋ ሰውን በእንባ አራጨው ስጨርስም ብዙወቹ ማሻአላህ እያሉ ግንባሬን ይስሙኝ ነበር
.......ይህን ሳደርግ እድሜየ ገና 17 ነበር ታዲያ በዚህ ኡስታዝ ተርቢያ እየተደረግን ማን ይቻለን ለኢስላም ፍቅሩ አደረብን መስጊድ የማይመጡ ቁርአን ያልቀሩትን ማበረታታት ተያይዘንዋል፡፡ ቅዳሜና እሁድ በረፍት ጊዜያችን ሪህላ በየሰፈሩ ቤት እየቆረቆርን ዳእዋ እናደርጋለን
     አስታውሰዋለሁ አሪፍ ጊዜ ነበር ትምህርት ቤት በእረፍት ሰአት ዳእዋ ፕሮግራም ይዘን ከጓደኛየ ኑረዲን ጋር እየተቀያየርን ዳእዋ እናደርጋለን ኑረዲን ከእኔ በእድሜ ከፍ ይላል ሰለምቴ ነው የድሮ ስሙ ኤፍሬም ይባላል፡፡ ሴት ወንዱ ሙስሊም ክርስቲያኑ የትምህርት ቤት መስገጃ ቦታ ተሰባስቦ ዳእዋችንን ይሰሙ ነበር ሱሪ የለበሱ ክርስቲያን ሴቶች ሳይቀሩ ይታደማሉ ዳእዋው ሲያስለቅስ አብረው ያለቅሳሉ ምን አይነት አሪፍ ጊዜ ነበር ታዲያ በዚያን ጊዜ ፍቅር የማይታሰብ ነው፡፡
    አስታውሳለሁ ከትምህርት ቤት ስለቀቅ ከኛ ሰፈር በታች አዚዛ የምትባል ልጅ ልትተዋወቀኝ ፈልጋ አዚዛ እባላለሁ ስትለኝ ከክላስ የሮጥኩኝ ቤቴ ገባሁ፡፡ ላየኝ ሰዉ የመቶ ሜትር እሯጭ ወይም የማራቶን ተወዳዳሪ ነበር የምመስለዉ፡፡ መቅሰፍት የወረደብኝ እስኪመስለኝ ሴቶች አሰላሙ አለይኩም ቢሉኝ እንኳ ላብ በላብ ነበር የምሆነዉ፡፡ ሴት ጋር ወሬ ቀጥ ብሎ ማየት በጭራሽ አይታሰብም ፡፡ ቂራአትና ዳእዋ ትምህርት ብቻ ነበር እንቅስቃሴያችን
   አልሃምዱሊላህ ይህ ሁሉ የአላህ ጸጋ ነው ኡስታዝ ጀማልንም ሳላመሰግነው አላልፍም አብሶ አንድ ጊዜ ረመዳን ወር ላይ በ 27 ኛው ለይል ታላላቅ ኡለሞች ሳይቀር ዳእዋ ለማድረግ ፈልገው ሲቋምጡ ዛሬ ተረኛው ከድር ነው ብሎ ሚንበሩ ላይ እጀን ይዞ ያስቀመጠኝን አልረሳውም፡፡ እንደዚህ አይነት የአኼራ ወንድም የትም አይገኝም ብዙ ነገር በህይወቴ አበርክቶልኛል
   እሁድ ረፋድ ላይና ጅሙአ ከመግሪብ በኋላ መስጅድ ዳእዋ ፕሮግራም ይዞልኝ አደርግም ነበር ሁልጊዜ ለአላህ ብየ ስወደው እኖራለሁ፡፡ ከቂርአቴም ጎን ትምህርቴንም እየተማርኩ ነዉ 10 ኛ ክፍል ማትሪክ ተፈተን ውጤቱ ሲመጣ ግን ....

#part ➋ይቀጥላል

join
@analmuslimi