Get Mystery Box with random crypto!

የተማሪ መልሶ ቅበላ ማስታወቂያ ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በ | አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

የተማሪ መልሶ ቅበላ ማስታወቂያ

ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ :-

በኮቪድ-19 ምክንያት የተቋረጠውን የ2012 ዓ/ም የ2ኛ ሴሚስተር ትምህርት ለመጀመር ዩኒቨርሲቲው ስለወሰነ የመጀመሪያ ድግሪ ተማሪዎች
1. በ2012 ዓ/ም የዋናው ግቢ 2ኛ-4ኛ ዓመት፣ የኩልፎ ካምፓስ 2ኛ-3ኛ ዓመት፣ የዓባያ ካምፓስ 2ኛ-3ኛ ዓመት፣ የጫሞ ካምፓስ 2ኛ-3ኛ ዓመት፣ የሳውላ ካምፓስ 2ኛ-4ኛ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት የማድረጊያ ጊዜ ከየካቲት 4-6/2013 ዓ/ም ሲሆን ትምህርት የካቲት 8/2013 ዓ/ም እንደሚጀመር እንዲሁም
2. የሁሉም ካምፓሶች የ2012 ዓ/ም የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት የማድረጊያ ጊዜ ከየካቲት 16-18/2013 ዓ/ም ሆኖ ትምህርት የካቲት 22/2013 ዓ/ም የሚጀመር መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በአፅንዖት ያሳውቃል፡፡

ማሳሳቢያ፡-

• በ2012 ዓ/ም 2ኛ ሴሚስተር ኢንተርንሽፕ ላይ የነበራችሁ 4ኛ ዓመት የውሃና የሌሎች ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደ ፊት የሚገለፅ ይሆናል፡፡
• በጉዞ ወቅትና ወደ ካምፓስ ስትገቡ ለኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄ የምትጠቀሙት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
• ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
@amuminimedia