Get Mystery Box with random crypto!

አንቺ ግን ምንድነሽ? ===+==+====== በድምፅሽ ወላፈን አካላቴ ሲዝል፤ በሳቅሽ ነዳድ አይኔ | ፅሁፍ በኑሀሚን

አንቺ ግን ምንድነሽ?
===+==+======

በድምፅሽ ወላፈን አካላቴ ሲዝል፤
በሳቅሽ ነዳድ አይኔ ሲንቀለቀል፤
በቃልሽ ነበልባል ልቤ ሲንጠለጠል፤
ደግሞ ትሔጃለሽ እጅሽን ያዝኩ ስል።

አንቺ ግን ምንድነሽ?
ቡዳ፣ ነሽ ሰላቢ፤
ልቤን ቆልፈሽ ሌላ ማታስገቢ።
አንቺ ግን ምንድነሽ?
መልስ ብቻ ስጪኝ፤
ወይ ሌላ ላስገባ ከልቤ ውጭልኝ።

ውጭልኝ እልና ሲባባብኝ ሆዴ፤
ሳስብሽ ደግሞ አይቀርም መንደዴ።
እኔንጃ አላቅም ፈፅሞም አልገባኝ፤
ምን አይነት ፍቅር ነው እኔን የከተበኝ።


ከአፍሽ የሚወጣው ቃል
ነፍስ ይዘራል፤
አንቺ ግን ምንድነሽ?
ነፍሴን ነጥቀሽኛል።
ሰላቢ ነሽ ቡዳ፤
ልቤን ሰውረሽ ምታሳይኝ ፍዳ።

በሕልሜ ማልምሽ፤
ነጋ ጠባ ልቤ ሚያስብሽ፤
አንቺ ግን ምንድነሽ?

ምንተስኖት ሱሌይማን
ቀን፦21/05/2015
@getami_mintesnot

አስተያየት
@mintesnot_suleyman