Get Mystery Box with random crypto!

ከእኔነቴ ጀርባ ከሳቄ ባሻገር እሷነነቷን ነስታ ለማኖር የምትጥር አንዲት ብርቱ እንስት ከጎኔ ተቀ | የሶላ ደብዳቤ

ከእኔነቴ ጀርባ ከሳቄ ባሻገር
እሷነነቷን ነስታ ለማኖር የምትጥር
አንዲት ብርቱ እንስት
ከጎኔ ተቀምጣ ስታየኝ በስስት
ችግሬን ረስቼ አገኘሁኝ እረፍት
የምኞቴ ልኬት
ሳስደስታት ማየት፣
የሷ ትልቅ ፀሎት
እኔን አለማጣት
ታዲያ...
ለዚህች መልከ መልካም
እራሴን ባላጣም
ደስታዋን ወስጄ ሀዘኔን ብሰጥም
ከሷ ተለይቼ
መኖርን አላውቅም
.
መኖሯን አይቼ አለሜ የምላት
ከሁሉ የምትልቅ አለችኝ ወርቅ እናት
.


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters