Get Mystery Box with random crypto!

ለውዴ ውዱ ነሽ በጎደለ ሞልተሽ፤ በጠፋው ተክተሽ፣ ሲዝል አበርትተሽ፤ ግራውን ደግፈሽ፣ የብቸኝነ | Amleset Muchie

ለውዴ ውዱ ነሽ

በጎደለ ሞልተሽ፤ በጠፋው ተክተሽ፣
ሲዝል አበርትተሽ፤ ግራውን ደግፈሽ፣
የብቸኝነት ጉዞውን፤ በጥንድ ቀይረሽ፣
ባብሮነትሽ አጅበሽ፤
ሙሉ አደረግሽው፤ መልኩን አሳቅፈሽ
እራሱን ደግመሽ፣ እራስሽን ደግመሽ።

መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ሚካኤል እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ብሩክቲ እናት?
ሁሌም አብራው ያለች፤ እየሆነች ብርታት፣
ለብላቴናው ክብሩ፤ ለልቡም ዘውድ ናት።

እንደ ግጥሜ ርዕስ፤ እንደ ስንኝ ቋጠሮ፣
እንደ ጠቢብ ቅኔ፤ እንደ ፀሐይ ኑሮ፣
ልብሽ ብሩህ ነው፤ ዘውትር የሚፈካ፣
መልክሽ በለስ ነው፤ ውዴ ባንቺ 'ረካ።

የሰጠሽው ፀጋ፤ የሰማይ ላይ መና፣
እንደ ምድር ሃመልማል፤ የፈካ ነውና፣
ልቡን ፍቅር ሞላው፤ ደስታውም አበበ፣
ለውዴ ውዱ ነሽ፤ በመልክሽ ተዋበ!

እንደ ከዋክብ ብዙ፤ እንደ ጀምበር ውብ፣
አንድ ሰው እልፍ ነው፤ ከተቸረው ልብ!!
አንድ ሳለሽ ብዝተሽ፤ ሁሉን የሆንሽለት፣
ጤና ይስጥሽ አምላክ፤ ዘላለም ኑሪለት!

እንደ ምድር አሸዋ፤ እንደ አባይ ጅረት፣
አንድ ሰው ብዙ ነው፤ ፍቅር ከሞላበት!
በዝተሽ አበዛሽው፤ በርተሽ አፈካሽው፣
ከፊትም ከኋላም፤ በሁሉም ከበሽው።

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/