Get Mystery Box with random crypto!

የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም ከሰሞኑ በምድረ አሜሪካ ኦሪገን ግዛት ተካይዶ በነበረው 18ተኛው | Amleset Muchie

የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም ከሰሞኑ በምድረ አሜሪካ ኦሪገን ግዛት ተካይዶ በነበረው 18ተኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተቀዳጀነው አንፀባራቂ ድል የተሰማኝን ደስታ ስገልፅ በተለይም በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ብሔራዊ ስሜታችን ሊጠናከር በሚገባበት በእዚህ ታሪካዊ እና ወሳኝ ሰዓት ይህን አኩሪ ድል ላስመዘገቡ ባለውለታ ውድ ጀግኖች አትሌቶቻችን እና እንዲሁም ይህ የተቀናጀ ውጤት እንዲመጣ ከፍተኛ አስተዎፆ ላደረጉ ጀግናዋ አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ለአሰልጣኞች እና ለመላው የሉካን ቡድኑ አባላት በሙሉ ከፍ ያለ የአክብሮት ምስጋናዬን እያቀረብኩ ነው::

በእዚህ አጋጣሚ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)