Get Mystery Box with random crypto!

ሥነ-ግጥም

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharic_poems — ሥነ-ግጥም
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharic_poems — ሥነ-ግጥም
የሰርጥ አድራሻ: @amharic_poems
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.22K
የሰርጥ መግለጫ

____________________
ማንኛውንም ሃሳብ በ @Amharicpoembot ይላኩልን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-02-03 20:14:17 ተነሳና ... ... ተነስ


ቀልደኛ ገበሬ ሳይቀልድ፣
በሰኔ ወር እየሞተ፣
ሰኔና ሰኞ ገጥሞበት፣
ሀገሬው እያቃሰተ።

እያየህ በየጎዳናው፣
እያየህ ባደባባይ ላይ፣
ከምድር አረንቋ በዝቶ፣
ከሰማይ ተከፍቶ ቀላይ፣
ባትፈረጅ ምን አለበት፣
ባትባልስ ክፉ ብቃይ።

አትነስ እንዳነሱቱ።

ለፍቶ አዳሪውን አታብግን፣
በተንኮል ከዘሩት ማሳ፣
ከሰዎች ጭዳ ሳትዘግን፣
ከራስህ ትንሽ ቀንሰህ፣
ላ'ገርህ በብዙ ወግን።

ልጅ እያለህ በጨቅላነትህ፣
ከመላእክት ስታወጋ፣
ፈገግ ብለህ ባደክበት፣
በእናት ባባትህ አልጋ፣
በ'ስተርጅና ጭንቀት ሳይሆን፣
ምሽታቸዉ አንጋ።

(ከ_ ሰለሞን ሳህለ
“ያ'ፍቃሪ ሰው ትንፋሽ” የግጥም መድብል ላይ የተወሰደ)


@amharic_poems
6.3K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-02 20:31:22 ድርሳነ-አምሮት

በጠጣኹኝ ቁጥር አይቆርጥልኝ ጥሜ
በጎረስኩኝ መጠን አይበረታም ዐቅሜ
ምን ይኾን ምስጢሩ...?
ጉጉቴ እየበዛ ፣ የሚያስመኘኝ ዕድሜ?


(ተስፋኹን ከበደ
የሞት ጥቁር ወተት)


@amharic_poems
5.8K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-02 20:31:19 ሕልመኛ ተጓዥ

( . . . ተቀበል . . . )
በመንገድኽ ኹሉ ዕንቅፋት አትፍራ
ተማርበት እንጂ በእውቀት አትኩራ።

መውደቅኽ ምሳሌ ፣ ሸክፈው እንደጓዝ
ድሎትን አትውደድ ፣ የንዋይን ጉዝጓዝ።

ስሕተትኽን ግደፍ ፤ መርምር በረቂቁ
በመጠረቡ ነው ፤ አልማዝ ማብሩቅረቁ።

የጅራፍ ቁግ አጥብቅ ፤ ግመድ አታቅማማ
ካልገረፋት አይጮኽ ፣ ካልጮኽ አይሰማ።

ደዌን አትሽሸው ፣ መርምር በጽሞና
ከችግር አይደለ ወይ? መፍትሔ 'ሚጠና።
አስተውል ፣ ተመልከት! መርምር በአርምሞ
ማንም ሰው አይድንም! ካልታመመ ቀድሞ።
(ደዌን አትሽሸው ፣ ይልቅስ መርምረው
ከመታመም ሌይ ነው! መድኅን 'ሚገኘው።)

"የሕልሜ ሳቢሳ፤
ሾተልኽን አንሣ
ሊበላኝ ነበረ ፣ ቶሎ ባልነሣ።
የሕልሜ ነብር
ይበላኝ ነበረ ፣ ተንቼ ብቀር።"

ይህ ነው ያ'ንተ ግጥም !
ይህ ነው ያ'ንተ ዜማ !
በነቂስ አትመን . . . !
ግምትም አትጣ . . . !
ልብኽንም ስማ።
ይህ ነው ያ'ንተ ዜማ !
ይህ ነው ያ'ንተ ግጥም !
ያለ መስናክል፣
ያለ አንዳች ዕክል፣
ሕይወት ፍጹም አይጥም።

(ተስፋኹን ከበደ
የሞት ጥቁር ወተት)


@amharic_poems
5.9K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-01 20:36:18 አንድ ሰው

እሁድ ማለዳ ላይ...
ገላዋን ታጠበች
ልብሶቿን ለበሰች
ሽቶ ተርከፍክፋ ከጎዳና ወጣች

በመንገድ ስትጓዝ...

የፀጉሯን መዘናፈል የጡቷን መኮፈስ
የረጨችው ሽቶ ካደባባይ ሲነፍስ
እሷን ያየ ሁሉ ወንዱ ተጨነቀ
በደም በውበቷ እየተደነቀ
ያስተዋላት ሁሉ ዓይኑ መንገድ ሳተ
ከዳሌ ከጡቷ ሔደ ተከተተ።

ከቦታው ስትደርስ...

ወዳጇ አልመጣም
ሰአት አልጠበቀም
ለውበቷ አልሳሳም።
ሠዓት ገላመጠች
ፊት ኋላዋን ቃኘች
ማኪያቶ ደገመች
ዙርያዋ ባለው ሰው እጅግ ተናደደች
እልህ ልቧን ሞላ
ፊቷ ከደም ቀላ
የሚመኛት ሁሉም
ወንዶቹ በሞላ
የርሷ ልቧ ሌላ።

ሠዓቱ ረፈደ...

የጠዋት ደስታዋ ከሷ ተሰደደ
አይኖቿ ረጠቡ
አንድ ሰው አሰቡ
አንድ ሰው ተራቡ።

አንድ ሰው ነበረ እርሷን የናፈቀው
ያን ያልመጣውን ሰው
ዓይኗ የተራበው

(ኤፍሬም ስዩም)

@amharic_poems
5.8K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-31 20:30:05 “ሻሞ!”

ከራሴው ምናብ ውስጥ፤ ለራስ ይሉት ጊዜ
ሠጠሁ ያልኩኝ እለት፤ በዛ መሰል ጓዜ…

ሻሞ ነው ሃሳቤ፤ “ሻሞ” ነው ሕይወቴ
ለማግኘት ስሻማ፤ ያለኝን ማጣቴ…
ሻሞ ለሃይማኖት፣
ሻሞ ለማንነት፣
ሻሞ ለመሰደድ፣ ሻሞ ለምፅዓት
(ታከተኝ መሻማት....)
ፍላጎት እንደሆን፣
በማጣት አይሞላ፣ በማግኘት አይጎድል
የወተት ጥርስ ነው፣ ተነቅሎ ሚበቅል።

(ኄኖክ ሥጦታው
መንገድ)

@amharic_poems
5.5K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-31 20:30:05 ጭምብል

በፈገግታ ተከልለን፣ የክፋት ጥርሶች ስናገጥ
እኩይ ሥራችን ገፅ ሆኖ፣
አድርጎናል መልከ-ቅይጥ።
“አስመሳይነት”
መንታ ስለት፣
በጥርስ ሞረድ ሲሞዠጥ
አንደበት በውሸት ሲከፈት፣ ገፅ በጭምብል ሲለበጥ
ሰይፍ ይወጣል ከአፎት፣ መልካም ልቦችን የሚቆርጥ።

Paul Laurence Dunbar
ውርስ ትርጉም ፦ ኄኖክ ስጦታው ናሁሰናይ

@amharic_poems
5.3K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-30 20:30:11 ጠላትን መለየት

አትርሳ!
የማለዳው አየር መታደስ ያዘለው፣
ሳይደክም የሚከንፈው ወደ አበቦችህ ነው።

የንቀት ግድግዳ
የጥላቻ ጥላ ገፍቶ ካልከለለው፣
እያንዳንዱ ውበት የራሱ አሽከር አለው።
ይኮተኩተዋል፣ያጥረዋል ሊያፈካው፣
ይሟገትለታል ቀጣፊ ሲነካው።

በል አንተ ብኩን አሽከር!
ዜማውን አትሰባብር ከቅኝቱ ግባ፣
በፀሐይ ቂም ይዘህ አትትከል አበባ።

(የመንስ ከፍታ
በረከት በላይነህ)

@amharic_poems
5.4K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-29 20:31:01 "ሐሙስ እንጋባ"


በዚህ በ'ኛ ዘመን ፥
ሰዉ ለሰው ላያስብ ፥ተጨካክኗልና
የዘመድ አዝማድ ሆድ፥
ል'ናዝል ፈረዱ ፥ፍቅራችን ሳይጠና።

የጠጪው እስክስታ፥
የበዪው ዳንኪራ ፥ ከሰርጋችን ቢቀር፤
አይፀና ይመስል ፥የቤታችን ማገር...
የዉርስ እርግማን ፥
የልማድ ሥርዓት፥ ሰቅዞ ይዞናል
ይኸው ባንደግስ፥
ጎጇ'ችን ባንድ ሌት ፥ይፈርስ መስሎናል።

በጠመቅሽው ጠላ፥ ወጋቸውን ሊያዩ፥
በጣልኩት ፍሪዳ ፥ትውስታ ሊያቆዩ፤
"ዓለምህ ዛሬ ነው" "ወግሽ ነው "እያሉ፥
በተስፋችን ሞረድ፥ጥርሳቸውን ሳሉ።

ወዴት እንሸሻለን?

እንታረድና፥
ቅሪላቸው ይሙላ፥ ጥማቸው ይረስርስ፥
ብቻ የሰርጉ ቀን፥
ይዘዋወርልን ፥ከእሑድ ወደ ሐሙስ።

እሁድ ሰንበት ሲሆን፥ ሐሙስ ስንብት ነው
በጌታ ትንሳኤ፥
በዓለሙ እረፍት፥
ነፍሳችን የሚዝል፥ የምደክም ምነው?
ምነው የምንደግስ?
ጎራሽ የምንጠራ፥
ጠጪ የምንቀጥር፥ በእለተ ሰንበት
ሀሙስ ይሁን እንጂ፥
እንደፈረደብን፥ እንደፈረደበት።

ሐሙስ ሲመሰጠር፥
"ሕጽበተ ሐሙስ" ነው ፥የመጨረሻ 'ራት
ጌታችን ኢየሱስ ፥
ከሐዋርያት ጋር ፥የተመገበበት

የተበደርነውን ፥
ጠጅ ሲጨልጡ፥ ፍሪምባ ሲያደቁ፥
ከሰርጉ በኋላ፥
እንደማንበላ ፥በዚያዉም እንዲያውቁ
ለደስታቸው ብለው ፥
ባበጁት ሥርዓት ፥ጉሮሮ እንደዘጉ
ዳግም የማንበላው፥
የመጨረሻ ራት ፥
መሆኑ ይግባቸው ፥ሐሙስ ይሁን ሰርጉ።

ባክሽ እንቀይረው፥
ሐሙስ እንጋባ ፥ይቅርብን የእሁዱ፤
ስጋችንን ቆርሰን ፥
ደማችንን ቀድተን፥
እንደጋበዝናቸው ፥ምናልባት ቢረዱ።

(ረድዔት አሰፋ)

@amharic_poems
5.6K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-28 20:30:09 አንቺን ነበረ

አበስኩ ገበርኩ ብያለሁ
በጾም ጡትሽን አይቻለሁ

በማማት ስወድቅ ስነሳ
ባንቺ ባየሁት አበሳ

ልቤ ተሰብሮ ካልቀረ
መስቀልስ አንቺን ነበረ!!!

(አበባው መላኩ
ከራድዮን-1999 ዓ.ም)

@amharic_poems
5.4K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-27 20:30:54 ጥበቃ 1
·
ይረዝምብኝና የመምጫሽ ቀን ቁመት
እንቅልፍ በወሰደኝ
እላለሁ ላንድ አመት፡፡
·
ጥበቃ 2
·
ስንት ዓመት አልፎ ነዉ
ምን ያህል ስንት ዕድሜ
ሣር የበቀለብኝ ስጠብቅሽ ቆሜ፡፡
·
ኑረዲን ዒሣ
(መደድ)


@amharic_poems
5.5K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ