Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ተመስገን ዳናን አሰናብቷል !! በዘንድሮ የውድድር አመት ባደረጋቸው 10 | Amhara Sport

ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ተመስገን ዳናን አሰናብቷል !!

በዘንድሮ የውድድር አመት ባደረጋቸው 10 ጨዋታዎች 4 አሸንፎ በተመሳሳይ 4 ተሸንፎ 2 ጨዋታ ብቻ በአቻ ዉጤት ያጠናቀቀዉ ኢትዮጵያ ቡና በአስራ አንደኛዉ ሳምንት በትላንት ዕለት በሀድያ ሆሳዕና 1ለ0 በሆነ ዉጤት በተሸነፈ በማግስቱ አሰልጣኙን አሰናብቷል።

ይሄንንም ተከትሎ ዛሬ ከሰዓት የኢትዮጵያ ቡና አመራሮች በአስቸኳይ ስብሰባ ለአሰልጣኙ የስንብት ደብዳቤውን እንደሚሰጡት ተገልጿል። ኢትዮጵያ ቡና በ14 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

@amharasport