Get Mystery Box with random crypto!

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 9ኛ ሳምንትና የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ | Amhara Sport

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 9ኛ ሳምንትና የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 9ኛ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች ስድስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሁለት ጨዋታ ያለግብ በአቻ ሲጠናቀቁ 19 ጎሎች በ16 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። የጎሎቹ አገባብ አንድ በፍፁም ቅጣት ምት ቀሪዎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው። በሳምንቱ 28 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ አንድ ተጫዋች ሁለተኛ ቢጫ በማየቱ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥተዋል።

የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ህዳር 17/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በተጫዋች ብርሀኑ አሻሞ(ሃዋሳ ከተማ) ክለቡ ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ጨዋታ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ተወስኗል::

በክለቦች መቻል በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ አምስት ተጫዋች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

@mandurasport