Get Mystery Box with random crypto!

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 8ኛ ሳምንትና የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ | Amhara Sport

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 8ኛ ሳምንትና የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 87ኛ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች አምስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሶስት ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቅ 23 ጎሎች በ22 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። የጎሎቹ አገባብ አምስት በፍፁም ቅጣት ምት አንድ በራስ ላይ ቀሪዎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው። በሳምንቱ 35 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ አንድ ተጫዋች በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥተዋል።

የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ህዳር 11/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በተጫዋች መክብብ ደገፉ(ሲዳማ ቡና). ክለቡ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው ጨዋታ የተጋጣሚን ቡድን ግልፅ ግብ ዕድል በማበላሸት ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል።
በክለቦች አርባምንጭ ከተማ እና ፋሲል ከነማ በሳምንቱ ጨዋታ የክለባቸው አምስት ተጫዋች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡

@amharasport