Get Mystery Box with random crypto!

ከቆቦ በሰሜን ወሎ ቆቦ ከተማ አብዛኞቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ስራ እንዳልጀመሩ ከስፍራው የሚገ | Amhara today

ከቆቦ
በሰሜን ወሎ ቆቦ ከተማ አብዛኞቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ስራ እንዳልጀመሩ ከስፍራው የሚገኙ የመረጃ ምንጮች ገለፁ።

ሰሞኑን በፋኖ እና መከላከያ ሰራዊት መካከል የነበረውን ውጊያ ተከትሎ በቆቦ ከተማ የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል። ላለፉት
አራት ቀናት ግን ሰሞኑን የነበረው ተኩስ በመቆሙ የከተማዋ እንቅስቃሴ ወደ መደበኛው ቢመለስም አብዛኞቹ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። በዚህም አብዛኞቹ አመራሮች የት እንደሄዱ አይታዎቅም ብለዋል። እንደ መረጃ ምንጮቹ ከሆነ ሸሸተዋል ወይም ተደብቀዋል ብለዋል። በተመሳይ የቆቦ ከተማ የከንቲባው መኖሪያ ቤትም ከትናንት በስተያ በጥይት ተደብድቧል ብለዋል።

ከቀስቱ ስር በመጫን በቪዲዮ የተደገፉ መረጃዎች በነፃ ይመልከቱ