Get Mystery Box with random crypto!

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አብሮነቱን ለማስቀጠልና ለማጠናከር የህዝብ ለህዝብ ምክክር እያካሄደ ነው። | Amhara Media Corporation

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አብሮነቱን ለማስቀጠልና ለማጠናከር የህዝብ ለህዝብ ምክክር እያካሄደ ነው።
ባሕር ዳር፡ ጥር 23/2013 ዓ.ም (አብመድ) የህዝብ ለህዝብ ምክክሩ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ማክሰኞ ገበያ ነው እየተደረገ የሚገኘው። በውይይቱ ከዳባት፣ ከታች አርማጭሆ፣ ከምዕራብ አርማጭሆ፣ ጠለምትና በሰቲት ሁመራ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች የተወጣጣ ህዝብ ተሳታፊ ነው።
የውይይቱ ዓለማ ከ1984 ዓ.ም በፊት ጀምሮ የነበረውን የአካባቢውን ባህልና ወግ ወደ ነበረበት መልሶ ለማስቀጠል ያለመ ነው።
የውይይቱ ተሳታፊዎች የህወሃት አገዛዝ ቡድን ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብን አንድነቱን በማዳከም ያለ ማንነቱ ማንነት፣ ያለ ባህሉ ባህል ሰጥቶ ታሪኩንና ወጉን እያጠፋ በደል ሲያደርስ እንደቆየ አንስተዋል።
አሁን ላይ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የተገኘውን ድል እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ አንድነቱን አጠናክሮ የልማት ተጠቃሚ ለመሆን ዝግጁ እንደሆነም በውይይቱ ተገልጿል።
የልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅፋት ናቸው ያሏቸውን እንደ ግድያና ስርቆት መሰል ሕገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልም ተወያዮቹ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ዘጋቢ፡- ኀይሉ ማሞ - ከወልቃይት
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m