Get Mystery Box with random crypto!

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለሩሲያ መንግሥት ልዩ እውቅና ሰጠ። ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2015 ዓ.ም ( | Amhara Media Corporation

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለሩሲያ መንግሥት ልዩ እውቅና ሰጠ።

ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞው የሶቬት ኅብረት የአሁኗ ሩሲያ ለባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ መመሥረትና ዘመናዊ ትምህርት በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጋለች።

በዘመነ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የቀድሞዋ ሶቬት ኅብረት የአሁኗ ሩሲያ በሀገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም እንዲገነባ ከፍተኛ ድጋፍ አድርጋለች።

ዩኒቨርሲቲው ለሩሲያ የሰጠውን እውቅና በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ትርኪሂን ተቀብለዋል።

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለ44 ሀገራት ኤምባሲዎች፣ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽንና ለሌሎች የሚዲያ ተቋማት፣ ለተለያዩ ተቋማት፤ ለቀድሞ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ሰጥቷል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck