Get Mystery Box with random crypto!

'የቀድሞ የአማራ ልዩ ሀይልን መልሶ የማደራጀት ተግባር በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ ነው' የአማራ ፖሊ | Amhara Media Corporation

"የቀድሞ የአማራ ልዩ ሀይልን መልሶ የማደራጀት ተግባር በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ ነው" የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን

ባሕር ዳር ፡ ግንቦት 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገሪቱ የሕዝቦቿን ሠላምና ደህንነት እንዲሁም የማትደፈር ሉዓላዊት ሀገር ለማድረግ ጠንካራ መሠረት ያለዉ የፀጥታ ሀይል መገንባት አስፈላጊ መሆኑ ይታወቃል።

መንግሥት የፀጥታ መዋቅሩን እንደገና ለመደራጀት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

በአዲሱ መመሪያ መሠረት የክልል ልዩ ሀይሎችን በፖሊስ እና በፌዴራል የጸጥታ መዋቅር በማደራጀት ሂደት ውስጥ የአማራ ክልል ልዩ ሀይልም መንግሥት ባስቀመጠው አማራጭ የክልሉን የፀጥታ መዋቅር ለመቀላቀል ምርጫቸውን ያደረጉ አባላት ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል ገብተው የተሀድሶና መልሶ ማደራጀት ስልጠናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

ስልጠናውን የተሳካ ለማድረግ የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ በማሰልጠኛ ማዕከላቱ አስፈላጊውን ጥረት አያደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ሲል የዘገበው የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck