Get Mystery Box with random crypto!

'የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መስፈን እያከናወነች ያለውን | Amhara Media Corporation

"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መስፈን እያከናወነች ያለውን ተግባራት አጠናክራ ትቀጥላለች" ቅዱስ ሲኖዶስ

ባሕር ዳር: ግንቦት 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መስፈን እና ለምዕመናን ደኅንነት እያከናወነች ያለውን ተግባራት አጠናክራ እንደምትቀጥል የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ገለጸ።

ዓመታዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጉባዔው በተጀመረበት ወቅት እንደገለጹት፣ ቤተክርስቲያኗ ከመንፈሳዊ ተግባራት ጎን ለጎን የሰላም፣ የዕርቅ እና ሌሎች ዕሴቶችን ለምዕመኑ የማስተማር ሥራዎች እያከናወነች ትገኛለች።

ይህንን ተግባሯን በማጠናከር አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን የቤተክርስቲያኗ አባቶች ተግተው ሊሠሩ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት እና መግባባት መፍታት ይገባልም ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ በቤተክርስቲያኗ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጠቁመዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO