Get Mystery Box with random crypto!

በአሜሪካ ኦሪጎን እየተካሄደ በሚገኘው አስራ ስምንተኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ ሜ | አማራ ባንክ Amhara Bank √

በአሜሪካ ኦሪጎን እየተካሄደ በሚገኘው አስራ ስምንተኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ ሜዳልያ ደረጃ ሰንጠረዡ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

እስካሁን ኢትዮጲያ በውድድሩ አስር ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። አራት ወርቅ፣ አራት ብር እና ሁለት የነሀስ ሜዳልያዎች እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች ተገኝቷል።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚውን ደረጃ በመያዝ እየመራች ትገኛለች ። ኬንያ በስምንት ሜዳልያዎች ከአፍሪካ የሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሀገር ስትሆን ዩጋንዳ በሁለት ሜዳልያ ሶስተኛ ሆናለች።

ዘጠኝ የወርቅ፣ ሰባት የብር እና አስር የነሀስ ሜዳልያዎችን ያገኘችው የውድድሩ አዘጋጇ ሀገር ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካን የአለም ሜዳልያ ሰንጠረዡን በበላይነት እየመራች ትገኛለች።

የነገውን የወንዶች የ5000 ሜትር እና የሴቶች 800 ሜትር የፍፃሜ ውድድሮችን ሳይጨምር ኢትዮጵያ እስካሁን ከተሳተፈችባቸው የአለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና መድረኮች ኦሪገን ብዙ ወርቅ (4 *) የተገኘበት ውድድር ሆኗል::