Get Mystery Box with random crypto!

ቆቦ መብራት ካገኘች ድፍን አንድ አመት የራያ ቆቦ ወረዳ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተቋረጠ | አማራ ባንክ Amhara Bank √

ቆቦ መብራት ካገኘች ድፍን አንድ አመት
የራያ ቆቦ ወረዳ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተቋረጠባቸዉ አንድ ዓመት ተቆጠረ።
በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተቋረጠባቸዉ አንድ ዓመት እንደሆነው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡የራያ ቆቦ ወረዳ ውጊያ ከነበሩባቸዉ አካባቢዎች አንዱ ነው። አንድ የቆቦ ከተማ ነዋሪ እንደተናገሩት በከተሞቹ ኤሌክትሪክ ባለመኖሩ በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ደርሰውባቸዋል።
“መንግስት ምን እያለ ነው ፣ ሌላው ምን እያለ ነው ብሎ መረጃ ማግኘት አልቻለም ከቴሌቪዥን። የእንጨት ሥራ የብረታ ብረት ሥራዎች የሉም ቆመዋል ፡፡ ከርሰ ምድር ውሐም በመብራት ነው የሚወጣው፣ከዚህ ከፍተኛ የመስኖ ስራ አለ፣ የዚህ የቲማቲም የሽንኩርት፣የማሾ ከፍተኛ ምርት አቅራቢ ነው፣ የከርሰ ምድር ክልሉ ከፍተኛ በጀት በጅቶ ብዙ ሔክታር መሬት የለማ አለ፣ ያንን ሙሉ በሙሉ ሶስት ጊዜ ያመርት ነበር አሁን ሙሉ በሙሉ ቆሟል።»
የኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያገኙ ከተሞች ደግሞ ጥቂት የሚባሉ አይደሉም።
« ቤት ውስጥ ገብተህ ለመብራት የምንጠቀመው ማገዶ እንጨት ነው፣ አልተቻለም፣ በቃ ሁሉን ነገር ከሰል ገዝተህ ነው፣ እንጨት ገዝተህ ነው። ሰው በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ተቸግሯል፡፡ በራያ ቆቦ ወረዳ ውስጥ ሮቢት የሚባል ከተማ አለ፣ ጎብዬ፣ ዞብል እና ወርቄ ከተሞች ናቸው።
ይባስ ብሎ በዛ አካባቢ የነበሩ የመብራት ሃይል ሰራተኞች ወደ ሌላ ቦታ ተዘዋውረዋል ብለዋል።
======================