Get Mystery Box with random crypto!

አሁናዊ መረጃ ከስፍራው! በወልቃይት በረከት እና ሉግዲ መሃከል ትናንት በረድ ብሎ የነበረው ጦርነ | Abissiniya Empire #አማራ

አሁናዊ መረጃ ከስፍራው!

በወልቃይት በረከት እና ሉግዲ መሃከል ትናንት በረድ ብሎ የነበረው ጦርነት ዛሬ ሌሊት 9 ሰዓት በድጋሚ ጀምሮ  እስከ ረፋዱ 3 ሰዓት ድረስ በከባድ መሳሪያ የታገዝ ጦርነት ተካሂዷል።

የትህነግ ጦር አስቀድሞ ከሰራቸው 5 ባለ ሶስት ደረጃ  ምሽጎች ውስጥ ሶስቱ ተሰብረዋል። የተቀሩትም በቀጣይ 24 ሰዓታት ውስጥ እንደሚሰበሩ አሁን ያለው ጦርነት ምስክር ነው። መከላከያ ሰራዊቱ እና ልዮ ኃይሉ በጥምር እያጠቁ ነው። ከሁመራ ከተማ 25 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነው ጦርነቱ በማይካድራ አቅጣጫ እየተካሄደ ያለው።

ፋኖ፣ሚሊሻውና የአካባቢው ታጣቂ በቅርብ እርቀት ላይ ቢሰፍርም እስካሁን እንዲገባ አልተፈቀደም። ማይካድራን ጨምሮ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ከተማ ሁመራ በፋፁም መረጋጋት እና ሰላም ትገኛለች።