Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ተማሪዎች ማህበር [አተማ]

የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_students_association — የአማራ ተማሪዎች ማህበር [አተማ]
የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_students_association — የአማራ ተማሪዎች ማህበር [አተማ]
የሰርጥ አድራሻ: @amhara_students_association
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.94K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ አማራ ተማሪዎች መብት እንታገላለን

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-25 20:36:02
የህወሓትና የህወሓት አክቲቪስቶች አሁን ያሉበት ሁኔታ

ጠላት እንዳይሰማ(ኢትዮጵያዊያን) ብለን ዝም ብንል መሪዎቻችን ይተኛሉ ። ችግሮቹን በአካል ተገኝተን ብንናገርም እሚሰማን አካል የለም። እዚህ መጥተን( FACE BOOK) ብንናገርም ለጠላት አሳልፋችሁ ሰጣችሁን ይባል እና እንደ ጠላት ተቆጥረህ ይዘመትብሀል። ታዲያ ዝም ይሻላል?

ፍፁም ብርሀነ ከመቀሌ ዛሬ FACE BOOK ገፁ ካጋራው የተወሰደ። የጁንታው ቡድን ለማንም የማይጠቅም መሰሪ ቡድን መሆኑ አንዱ ማሳያ ቀንደኛ ደጋፊዎቹም እየተቃወሙት መሆኑ ነው።
1.1K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 19:55:05 በአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በጦርነቱ ምክንያት ተጨማሪ ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ የተወሰነላቸው ተማሪዎች ዝርዝር!

https://t.me/Amhara_students_association
1.1K viewsedited  16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 22:38:25
" አብን በጠቅላላ ጉባዔው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደመረጠ ተደርጎ የሚሰራጭ መረጃ ሐሰት ነው " - አቶ ጣሂር መሐመድ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባለፉት ሁለት ቀናት የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን አካሂዷል።

ዛሬ ደግሞ ሦስተኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።

የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጣሂር መሐመድ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሰጡት ቃል ፤ ትናንት በነበረው #የማዕከላዊ_ኮሚቴ_ስብሰባ በተወሰነ መልኩ የአመራር ሽግሽግ ለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች እልባት መሰጠቱን ገልፀዋል።

" ነገር ግን የፓርቲውን መመሪያ እና ደንብ በውል ካለመረዳት #በጠቅላላ_ጉባዔው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደተመረጠ የሚናፈሰው ወሬ ትክክል አይደለም " ሲሉ አብራርተዋል።

አቶ ጣሂር ጠቅላላ ጉባዔው የሚመርጠው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ነው ያሉ ሲሆን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የአገልግሎት ዘመን የሚጠናቀቅበት ጊዜ ደግሞ አልደረሰም ብለዋል።

በዚህም በማዕከላዊ ኮሚቴ የተላለፈ ውሳኔ በጠቅላላ ጉባዔ እንደተሻረ ተደርጎ በተለይ በማኅበራዊ የመገናኛ አውታር የሚንሸራሸረው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ አቶ ጣሂር መሐመድ በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ በጠቅላላ ጉባዔው ምንም አይነት የምርጫ ሂደት እየተደረገ እንዳልሆነ ከሰዓታት በፊት ገልፀዋል።

" ትላንት በተጠናቀቀው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባችን የአመራር መተካካቶችን አድርገናል። " ያሉት አቶ ጣሂር " አሁን ላይ የጠቅላላ ጉባዔያችን በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል " ብለዋል።
2.0K viewsedited  19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 22:25:57 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚማሩ የአማራ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ሥቃይ እና እንግልት አስመልክቶ ከአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) የተሰጠ መግለጫ!

በሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚማሩ የአማራ ተማሪዎች ላይ ከአድዋ በዓል ማግስት ጀምሮ ከፍተኛ ስቃይና እንግልት እንዲሁም የመብት ጥሰት እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡የጥቃቱ መነሻ <<ለምን የአጼ ምኒልክ ምስል ያለበት ወይም ንጉሡን የሚያስታውስ ቲ-ሸርት ትለብሳላችሁ?>> የሚል የድንቁርና እና ግብዝነትን ጥግ የሚያሳይ አሳፋሪ ምክንያት ነው፡፡

በተደጋጋሚ የምናስተውለው የታሪክ ክህደት ማንኛውም ታሪክ መሥራት የተሳነው እና የበታችነት ስሜት የሚሰማው ቡድን የሚያደርገው የተለመደ ተግባር ቢሆንም ይህ ጉዳይ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጥቃት ምክንያት መሆኑ በእጅጉ ያሳስበናል፡፡ይህንን ዘር ተኮር ጥቃት ከሌላው ለየት የሚያደርገው ሀገሪቱን የሚያስተዳድረው መንግሥት መቀመጫና የሁሉም ኢትየጵያዊ መኖሪያ በሆነቸው አዲስ አበባ የሚከናወን መሆኑ ነው፡፡በጥቃቱ በቁጥር ቀላል የማይባሉ ተማሪዎች ከመታሰራቸውም በላይ በርካታ ተማሪዎች የአካል ጉዳት እና የሥነ ልቦና ጉዳት ደርሶባቸዋል።በአሁኑ ሰዓትም ብዙዎቹ ከዩኒቨርሲቲው ውጭ በተለያየ ቦታ ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን ጥቂት ተማሪዎች ደግሞ ለደኅንነታቸው ምንም አይነት ዋስትና በሌለበት ሁኔታ በግቢው ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ወከባው በአማራ ክልል ውስጥም የአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) አመራሮችን በማሳደድ የተቀናጀ ሲሆን በዛሬው ዕለት የማህበሩ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ ታስሯል፡፡በመጨረሻም የፌደራል እና የክልሉ መንግሥት ተማሪዎች በማንነታቸው ተለይተው የሚደበደቡባት፣የሚፈናቀሉባት፣የሚታሰሩባትና የሚገደሉባት የጋራ ሀገር እንደማትኖረን ተገንዝቦ በአስቸኳይ የታሠሩትን እንዲፈታ እና የተማሪዎችን ሁለንተናዊ ደኅንነት በማረጋገጥ አጥፊዎቹን ለሕግ እንዲያቀርብ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡

መጋቢት 5 2014 ዓ.ም
የአማራ ትውልድ ተቋም!!!
1.8K viewsedited  19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ