Get Mystery Box with random crypto!

ቀይ ባህርም፣ አሰብም አሁን የግጭት ምንጭ ሊሆን አይችልም! 'አዲስ አበባ የእኛ ብቻ ነው' ብ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

ቀይ ባህርም፣ አሰብም አሁን የግጭት ምንጭ ሊሆን አይችልም!

"አዲስ አበባ የእኛ ብቻ ነው" ብለው ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ ከአፍሪካ መዲና ንፃሃንን እያፈናቀሉ ያሉት ገዥዎች "አሰብን በጦርነት እናስመልስ" እያሉ እየቀለዱ ነው!

ከሰላም ስምምነቱ በኋላም ትህነግ/ ህወሓት ሲፈነጭ ለአገር አደጋ ነውና አስቁሙት ሲባሉ "ጦርነት ናፋቂዎች፤ ሰላም የማይወዱ" ብለው የዘመቱት ኃይሎች ከጎረቤት አገር ጋር ጦርነት ካልገጠምን እያሉ ነው።

"ሸገር" ብለው ከሰየሙት ከተማ በራሱ አገር በመቶ ሺህ ህዝብ ያፈናቀሉ ነውረኞች፣ ወለጋ አገርህ አይደለም እንዳላሉን ስለ አሰብ የኢትዮጵያነት ሊቀሰቅሱ መጥተዋል።

ኧረ የፈጣሪ ያለህ!

ኤርትራና ኢትዮጵያ ሰላም ከፈጠሩ በኋላ የኤርትራን ወደቦች ለመጠቀም ንግግር ተደርጓል። ኤርትራ መንገድ ሰርታ ጨርሳ፣ የእናንተውን ክፈቱ ሲባል አይሆንም ያሉት የአራት ኪሎዎቹ ገዥዎቹ ናቸው። ምክንያቱ ደግሞ ለወደቦቹ በቅርብ ርቀት ያለው አፋርና አማራ ይጠቀማል በሚል ነው። በዚህ ጉዳይ ስብሰባ ተደርጎ "ይቅርብን" ያሉት ራሳቸው በቀጥታ ደንበር ስለሌላቸው ነው። አሁን አሰብ ወዘተ የሚሉት ለአገር አስበው እንዳልሆነ ማንም ያውቃል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ወደብ ነው ችግሩ? በአገሩ እንዳይኖር አድርጋችሁ፣ ወደ አዲስ አበባ እንዳያልፍ መንገድ እየዘጋችሁ፣ ከቀየው እያፈናቀላችሁ፣ የእምነት ተቋሙን እያፈረሳችሁ.... ወደብ እናስመልስ ልትሉት?

ካለፈው ጦርነት ሳያገግም በየቀየው ዘምታችሁበት፣ አስራችሁት፣ ማዳበሪያ እንኳን ማቅረብ ተሶኗችሁ፣ ባንኩን ባዶ አድርጋችሁ በሌላ አገር ስር ያለን ወደብ እናስመልስ ብትሉት ሊያምናችሁ?

ቀይ ባህርም አሰብም ወቅታዊ የህዝብ ጥያቄ አይደለም። ጥያቄው ቢነሳ እንኳን በሰላማዊ መንገድ ይነሳል እንጅ ህዝብ ጦርነት አይፈልግም። የጦርነት ፍላጎት የውጭ ኃይል ተላላኪነት ነው። ኢትዮጵያ ጦርነት በቃት አላላችሁም?

አዎ! ኢትዮጵያ ጦርነት በቃት!