Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ አባል እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለ ደሬ ወረዳ የመኢአድ እጩ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

በአዲስ አበባ የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ አባል እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለ ደሬ ወረዳ የመኢአድ እጩ ተወዳዳሪ መምህር መሀመድ ይማም በሀይቅ ፖሊሶች ታሰረ፤ ድብደባ እንደተፈጸመበትም ተገልጧል።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ሚያዚያ 22/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በአዲስ አበባ የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ አባል እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለ ደሬ ወረዳ የመኢአድ እጩ ተወዳዳሪ መምህር መሀመድ ይማም ሚያዝያ 21/2015 ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በሀይቅ ፖሊሶች መታሰሩን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከቤተሰብ ለምፕረዳት ችሏል።

መምህር መሀመድ ይማም በሀይቅ ከተማ ከንግድ ቦታው ባለበት 4 ፖሊሶች መጥተው በባለቤቱ እና በጎረቤቶች ፊት በመሳሪያ ሰደፍ እና በዱላ እየደበደቡ ወስደውታል ተብሏል።

አሁን ላይ በሀይቅ ከተማ ፖለስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል፤ ከቤተሰብ ጋርም እንዳይገናኝ ተከልክሏል።

እንድሪስ አሊ እና ራዕይ የተባሉ የመስኖ ፕሮጀክት ኃላፊዎች እና ሌሎች ወጣቶችም ከሰሞኑ በሀይቅ ከተማ የተደረገውን ሰልፍ አስተባብራችኋል በሚል ታስረው ይገኛሉ ሲሉ የሀይቅ ምንጮች ተናግረዋል።