Get Mystery Box with random crypto!

የ ኦሮሙማ ሰራዊት በኮምቦልቻ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የነበሩ 2 አማራዎችን ገደለ። ከ12 የሚበ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የ ኦሮሙማ ሰራዊት በኮምቦልቻ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የነበሩ 2 አማራዎችን ገደለ። ከ12 የሚበልጡ ተጎድተዋል

የአማራ ሚዲያ ማእከል
ሚያዝያ 3 2015 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

አምስተኛ ቀኑን በያዘው ህዝባዊ እንቢተኝነት ዛሬ ረፋድ ላይ በኮምቦልቻ ከተማ “የልዩ ኃይል አባላት የተያዙ አሉ” የሚል መረጃ በመሰራጨቱ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ግጭት ውስጥ መገባቱን ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ መግለጻቸዉን በመጠቆም ዘግባለች።

በኮምቦልቻ አንድ ጤና ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ የአዲስ ዘይቤ ምንጮች እንደገለፁት አንድ ሰው እዛው ተኩስ የተከፈበት ስፍራ ላይ ህይወቱ ማለፉን እና ሌላ አንድ ሰው በአምቡላንስ ወደጤና ጣቢያ እየተወሰደ ህይወቱ አልፏል ብለዋል።

በተጨማሪም 12 የሚሆኑ ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሚገልፁት ነዋሪዎች፣ አምቡላንስ በተደጋጋሚ ሲመላለስ እንደነበረና የተጎጂዎች ቁጥር ከፍ ሊል ይችላል ሲሉ ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት በኮምቦልቻ ከተማ ከመደበኛ ጊዜው የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ መኖሩን ነዋሪዎች ነግረውናል።ህዝባዊ እንቢተኝነቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።