Get Mystery Box with random crypto!

የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ ለሁሉም የአማራ ልጆችና ሀገር ወዳድ ለሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፥ በሀገራች | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ
ለሁሉም የአማራ ልጆችና ሀገር ወዳድ ለሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፥

በሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ፭ ዓመታት ጀምሮ ያለማቋረጥ በአማራ ሕዝብ የመኖር ተፈጥሮዊ መብት ላይ የብልጽግ/ኦነግ መንግሥት በወለጋና በአርሲ የዘር ጭፈጨፋ ተካሂዶባታል አሁን ደግሞ ትጥቅ ማስፈታት በሚል ሰበብ ጦርነት ታውጆበት ሕጻናትን በእድሜ የገፉ አረጋውያን ወንዶችና ሴቶችን በመጨፍጨፍ የመኖሪያ ቤቶችን ሳይቀር በከባድ መሣሪያ በማውደም ላይ ይገኛል።

ስለዚህ ይህንን በአማራ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማጋለጥ እንዲሁም የአሜሪካም ሆነ የአውሮፓ መንግሥት እጃቸውን እንዲያነሱልን ለማውገዝ ሰኞ Montag April 17,2023 (ሚያዝያ ፱ ቀን ፳፻፲፭) ዓ ም በፍራንክፈርት ከተማ
አሜሪካ ኮንስላት ፊት ለፊት ከቀኑ ፲፩ (11:00) ሰዓት ጀምሮ የተቃውሞ ሰልፍ ስለሚካሄድ በቦታው ትገኙ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን

ወደ ተቃውሞ ሰልፉ በባቡር ለመምጥት ለምንፈልግ ከ ፍራንክፉርት ባኖፍ (Frankfurt HBF) U-Bahn (U5) * Richtung *Preungesheim የሚለውን በመያዝ ከ ፩፭ (15ደቂቃ) በኃላ Gießner Straße የሚለው ፌርማታ ስንደርስ በመውረድ ትንሽ በእግር ተራምደን መዳረሻውን ማለትም የአሜሪካ ኢምባሲን እናገኘዋለን።

ከ ባኖፍ በተጨማሪ ከ አKonstablerwache U5 ን መያዝም ይቻላል።

በመኪና በቀጥታ ወደ ሰልፉ ቦታ መምጣት ለምትፈልጉ አድራሻው ይኸው

Americanisches Generalkonsulat

Gießener Str. 30, 60435 Frankfurt am Main

የአማራ ማኅበር በጀርመን