Get Mystery Box with random crypto!

የወለቴ ለ/ጽ/አ/ቅ/ሥላሴ ቤ/ክ ዐምደ ተዋሕዶ ሰንበት ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ amde_tewahedo_ss — የወለቴ ለ/ጽ/አ/ቅ/ሥላሴ ቤ/ክ ዐምደ ተዋሕዶ ሰንበት ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ amde_tewahedo_ss — የወለቴ ለ/ጽ/አ/ቅ/ሥላሴ ቤ/ክ ዐምደ ተዋሕዶ ሰንበት ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @amde_tewahedo_ss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 483
የሰርጥ መግለጫ

በሰንበት ት/ቤቱ የሚተዳደር ይፋዊ (Official) ገጽ።
“ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም።” ማቴ 4፥4 @Amde_Tewahedo_SS
https://www.facebook.com/AmdeTewahedoSS
#ዐምደተዋሕዶሰንበትትምህርትቤት #amdetewahedosundayschool

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-15 05:55:44 በቀላሉ ለማግኘት እነሆ

2014 ሐምሌ ሥላሴ ማኅሌት ቀጥታ ስርጭት

https://www.facebook.com/AmdeTewahedoSS/videos/739102197162614/

https://www.facebook.com/AmdeTewahedoSS/videos/1783549031976780/

https://www.facebook.com/AmdeTewahedoSS/videos/806325790524145/

ሐምሌ ሥላሴ በዓለ ንግሥ ( ታቦት ሲወጣ ጀምሮ ወረቦችን ወዘተ ያጠቃልላል

https://www.facebook.com/AmdeTewahedoSS/videos/589696509232761/

በአገልግሎታችን ላይ ለተባበራችሁኝ እግዚአብሔር ሥራችሁን ለዋጋ ያድርግላችሁ
26 viewsedited  02:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 05:23:02
ሐምሌ ሥላሴ ለምን ይነግሣል ?
ሥላሴ ለአብርሃም የመገለጣቸው ምስጢር ምን ይሆን ?
በአጠቃላይ ስለታሪኩ ለማወቅ አውርዳችሁ አንብቡት

አዘጋጅ ፦ ቃለአብ ብርሃኑ (ከደቡብ ኮሪያ )
172 viewsedited  02:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:01:13
118 views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 06:30:26
116 views03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 06:28:50 ለተሸላሚዎች የሞባይል ካርድ ልከናል እርሶም ለወደፊቱ አንብበው ይሸለሙ
ተሸላሚዎቹ እንዚህ ናቸው
➣ @Blentk6m
➣ @WAB_H
112 views03:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 07:54:27
118 views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 07:35:20 ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች ቀድመው ለመለሱ 2 ሰዎች የ 5 ብር ካርድ እንሸልማለን
# ጥያቄ (አንዱ ጥያቄ 5 ነጥብ ይይዛል)
1. የቅዱስ ጳውሎስን አይን ያበራለት ፣ ያጠመቀው ማነው ?
2. ንዋየ ህሩይ ምን ማለት ነው ?
3. ቅዱስ ጳውሎስ አይኑ ሳያይ ስንት ቀን ቆየ ?
4. ሳዉል በጌታችን ያመነው ጌታ ባረገ በስንተኛው ዓመት ነው ?
5. ቅዱስ ጳውሎስ ስንት መልዕክታትን ጻፈ?
6. ቅዱስ ጴጥሮስን እና ቅዱስ ጳውሎስን ያስገደለው ንጉሥ ማን ይባላል ?
7. ጴጥሮስ ምን ማለት ነው ? በግእዝ ፣ በዕብራይስጥ ምን ይባላል ?
8. የቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም ማን ይባላል ?
9.ቅዱስ ጴጥሮስ የት ተማረ ?
10. ቅዱስ ጴጥሮስ ስንት መልዕክታትን ጻፈ ?
ጉርሻ (ከ5)
# የ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤ/ክ አበባ የተ ቦታ ይገኛል ?
እስከ ማታ 2 ሞክሩ
114 viewsedited  04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 07:07:50 ከላይ ያለውን ጽሑፍ መሠረት ያደረገ ጥያቄ ይወጣል ጥያቄዎችን ቀደሞ ለመለሰ ሁለት ሰው የ 5 ብር ካር እንሸልማለን
# ከመልሱ ጋር ስልክ ቁጥሮን ስሞን ይላኩ በ commnent መጻፊያው ይጻፉ
116 views04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 07:05:19 # ቅዱስ ጳውሎስ

ጳውሎስ ማለት ነዋይ ህሩይ ማለት ነው። |ሐዋ 9:15| አንድም ብረሃን ማለት ነው
የቀደመ ስሙ ሳዖል ነው ሳዉል ማለት ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት ማለት ነው። ትውልዱም ከ ነገደ ብንያም ነው።(ፊሊ 3:5)አባቱም ዮስአስ ይባላል
የተወለደውም ጌታ ከተወለደ በ 5 ዓመት ሲሆነው በጠረሴስ ነው። ከ 5 ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም ተቀምጦ ከመምር ገማልያ ህገ ኦሪት ተምሯል።በወንጌል ያመነውም ጌታ በዐረገ በ10 ዓመት ነበረ ። ሳውል ክርስቲያኖችን የሚያሳድድ ነበር
ጌታም በደማቅ መበረቅ ተገልጦለት ሳዉል ሳዉል ስለምን ታሳድደኛለህ ብሎ ተናግሮታል ፤ እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ፦ ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ? አለው። ጌታም፦ ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል አለው።
፤ ከእርሱም ጋር በመንገድ የሄዱ ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንን ግን ሳያዩ እንደ ዲዳዎች ቆሙ። ሳውልም ከምድር ተነሣ፥ አይኖቹም በተከፈቱ ጊዜ ምንም አላየም፤ እጁንም ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አገቡት።
ሳያይም ሦስት ቀን ኖረ፤ አልበላምም አልጠጣምም። በደማስቆም ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ፥ ጌታም በራእይ፦ ሐናንያ ሆይ፥ አለው። እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ እነሆኝ አለ።ጌታም፦ ተነሥተህ ቅን ወደ ሚባለው መንገድ ሂድ፥ በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚሉትን አንድ የጠርሴስ ሰው ፈልግ፤
፤ እነሆ፥ እርሱ ይጸልያልና፤ ሐናንያ የሚሉትም ሰው ገብቶ ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቶአል አለው።
፤ ሐናንያም መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎች ሰምቼአለሁ፤በዚህም ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን አለው አለ።፤ ጌታም፦ ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና አለው።፤ ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፥ እጁንም ጭኖበት፦ ወንድሜ ሳውል ሆይ፥ ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፥ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ አለ።
፤ ወዲያውም እንደ ቅርፊት ያለ ከዓይኑ ወደቀ፥ ያን ጊዜም ደግሞ አየ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፥ ጌታችንም ከ 72 አርድእት አንዱ አድርጎታል ከዚያም በኃላ በ ክርስቶስ እመኑ እያለ አስተምሯል። ብዙዎችንም በክርስቶስ ሰም አስተምሮ አጥምቋኣቸዋል (ሐዋ14:10-18) በእስር ቤት በነበረበት ወቅትም ብዙ ሰዎችን አሰተምሮ አሳምኗቸዋል። ቅዱስ ጳውሎስ 14 መልዕክታትን ጽፏል ።
ከብዙ ተጋድሎ በኃላ በ 69 ዓ.ም ሲያስተምር ሄሮን ቄሳር አስጠሩት ሲል አዘዘ በንጉስ ፊት ሲቀርብ መሰቀሉን ይዞ ቀረበ ፤ንጉሱም ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡ አለ!!! በመጎናጸፊያውም ሸፍኖ ሰይፎታል ። ቅዱስ ጳውሎስም ሲያርፍ የ 72ዓመት አረጋዊ ነበረ። ከቅዱስ ጴጥሮስም ጋር ሰማዕትነት የተቀበሉትም በ አንድ ቀንና በአንድ ቦታ ነበር ። ይህም እለት ወርሃ ሐምሌ ቀን 5 ነበር ። የነዚህን ቅዱሳን በዓል ጾመ ሐዋርያት የሚፈታበት እንዲሆን አባቶች ሥርዓት ሠርተውልናል ። በዓላቸውም ታቦታቸው ባለበት ቦታ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ። ስለ እነዚህ ቅዱሳን ምልጃ ጸሎት ብሎ እግዚአብሔር ምሕረቱን ይላክልን!!!

ምንጭ፦➣ገድለ ሐዋርያት፣
➣ ዜና ሐዋርያት፣
➣ ነገረ ቅዱሳን ቁጥር
➣ መዝገበ ታሪክ ክፍል 2
➣ መጽሐፍ ቅዱስ

# አዘጋጅ አማረ አባይነ
114 viewsedited  04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 07:05:19 # ዝክረ ቅዱሳን ሐምሌ 5

ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት አረፉ

# ቅዱስ ጴጥሮስ
ቅዱስ ስምዖን የተወለደው በገሊላ ባህር ዳር በምትገኘው ቤተሣይዳ ነው።
(ማቴ 16:18) ጴጥሮስ ብሎ ስም ያወጣለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ስሙ ፦
በግእዝ ➣ ኰኲሐ ሃይማኖት
በዕብራይስጥ ➣ ኬፋ
በግሪክ (በጽር ቋንቋ )➣ ጴጥሮስ ማለት ሲሆን የሁሉም ትርጉም 'አለት' (መሠረት) የሚለውን ትርጉም ይይዛል (ማቴ 16 ፥ 18) ። የ አባቱ ስም ዮና ሲሆን ትውልዱም ከ ነገደ ሮቤል ነው።ዮና ከ ነገደ ስምዖን የምትሆን አንዲት ሴትን አግብቶ ቅዱስ ጴጥሮስን ወለደ ። ቅዱስ ጴጥሮስም ከተወለደ በኃላ እንደ ኦሪት ትእዛዝ መሠረት በስምንተኛው ቀን ወደ ግዝረት ቤት አግብተውት ሰሙን በ እናቱ ነገድ ስም ስምዖን ብለው ሰይመውታል።
ዕድሜውም አምስት ዓመት ሲሆን እነደ አይሁድ ሥርዓት ህገ ኦሪትን እየተማረ እንዲያድግ በቤተ ሳይዳ ወደ ምትገኘው ቅፍርናሆም ላኩት ። በዚኑ በባህር ዳር በምትገኘውና ታላቅ የንግድ ቦታ በሆነችው ቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረው ኢያኢሮስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት አሠርቶት በነበረው ምኩራብ እየተማረ አደገ ከዚያም በኃላ በዚያ ከተማ ቤት ሠርቶ ኮንከርድያ (ጴርጴቱዋ)የምትባል ሴት አግብቶ እነደ አባቱ ዮና ይተዳደርበት በነበረው ሥራ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ እና በመሸጥ ይተዳደር ነበር ።ጌታችን ዓሳ ከሚያጠምድበት ተጠርቶት ሐዋርያ ሐዋርያት አድርጎታል ማቴ 4:19 ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኃላ መዲናቸው ኢየሩሳሌም አንድ ዓመት ካስተማሩ በኃላ ወንጌል ካልደረሰበት ለማድረስ ዓለምን በዕጣ በተከፋፈሉ ጊዜ ርዕሰ ሐዋርያ ነውና ሮምን ደርቦ ደርሶቶታል። በሮምም ለ 25 ዓመታት አስተምሯል ከዚያ በፊት ግን በሠማርያ፣በልዳ፣በኢዮጴ ፣በአንጾኪያ፣ ጳንጦስ፣ በገላቲያ፣ በቀላጳዶያና እና በቢታንያ እስተምሯል።በ ትምህርቱም ሙታንን ከሞት አስነስቷል ።(የሐ ሥራ 9:32-34) ያስተማራቸው ምእመናንም ከሀይማኖታቸውእንዳይወጡ 2 መልክታትን ጽፎላቸዋል ።ንጉሱ ኔሮን ቄሳር የተባለ የሮም ንጉሥ ጣዖት አምላኪ ስለነበረ ። ለጣዖት እንዲሰግድ በአሰገደደው ጊዜም ለጣዖት አልሰግድም በማለቱ ንጉሱ ሊያስገድለው ከሮሜ መኳንንት ጋር ተማክሯል ። ይህን የሰሙ ምዕመናን እንዲወጣ ይነግሩታል እርሱም እንዳሉት ሲወጣ ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ወደከተማው ሲወጣ ያገኘዋል ። እርሱም 'ጌታዪ ወዴት ትሔዳለህ ' አለው ። ' ዳግመኛ ልሰቀል ወደ ሮሜ ከተማ እሔዳለሁ ' ብሎ መለሰለት ቅዱስ ጴጥሮስም ' ዳግመኛ ትሰቀላለህን' አለው ። ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌ ሳለ የነገረ ነገር አስተውሎ ወደ ከተማው ተመልሶ የሆነውን ለምዕመናን ይነግራቸዋል እነርሱም ይወዱት ነበረና እጅግ አዘኑ ።
ንጉሥ ኔሮን እንዲሰቅሉት አዘዘ ። ቅዱስ ጴጥሮስም ወታደሮችን እንዲህ ብሎ ይለምናቸዋል ' ጌታዬኢየሱስ ክርስቶስ ወደላይ ተሰቀለ እኔ ወደላይ ልሰቀል አይገባኝም ቁልቁል ልሰቀል ይገባኛል ' ብሎ ይለምናቸዋል ። እነርሱም እንደነገራቸው አድርገው ሰቀሉት ። በዚህች ዕለትም የሰማዕትነትን ክብር ተቀበለ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን ።
106 views04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ