Get Mystery Box with random crypto!

#ሥዕለት_ሰሚው_ሽማጎ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ••• እግዚአብሔር ይመስገን ሰው አላጣንም። ሰው በሌለለ | #የግጥም_ዓለም

#ሥዕለት_ሰሚው_ሽማጎ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ

•••
እግዚአብሔር ይመስገን ሰው አላጣንም። ሰው በሌለለበት ሰው የሆኑ ሰዎችን እግዚአብሔር አዘጋጅቷል። በገንዘብ መርዳት ስላልቻላችሁ እርዳታችሁ አያስፈልግም ማለት አይደለም ። ለሌሎች በማድረስ ከበረከቱ መሳተፍ ይቻላል። እመኑኝ ሙሉውን መሸፈን የሚችል ሰው ከመካከላችን ይኖራል። ሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ
#ጊዮርጊስ ቤቱን የሚሠራለትን ሰው አዘጋጅቷል። እናንተ Share ብቻ አድርጉ። ሌላ ነገር አላስቸግራችሁም። ደግሞ እኔ ችግራቸውን ስለማውቅ ነው እንጂ #በጎ አድራጊ አይደለሁም። ክርስቶስ በቸርነቱ የጠበቀኝ የኃጢአት ባርያ ነኝ። እናንተም በእኔ ቦታ ብትሆኑ የምታደርጉት ተራ ነገር ነው። የእናንተ ይህን ጽሑፍ አንብቦ እርዳታ ማድረግ ግን ትልቅ መታደል ነው።
•••
ዛሬ የምሥራች አለኝ። አንዲት እህቴ ስሟ
#ወለተ_ሕይወት ትባላለች። ራሷ ናት በቀጥታ የደወለችልኝ። የበኩሌን መርዳት እሻለሁ ብላለች። ስሟን ለመግለጽ የወደድኩት ጸሎት አድርጉልኝ ብላለች። ታዲያ ሰሞኑን ሱባኤ በመሆኑ ሁላችንም ውዳሴ ማርያም ፣ መዝገበ ጸሎት እንዲሁም መዝሙረ ዳዊት አድርሰን ስንጨርስ #ወለተ_ሕይወት በማለት ልናስባት ይገባል። በየ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ ያላችሁ እህት ወንድሞቼ ፤ እናት አባቶቼ ይህችን እህታችንን በጸሎት አስቧት። በተለይ በአካባቢያችሁ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የቅድስት ኪዳነምሕረት እና የቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የሚገኝ ከሆነ አደራ ለቀዳሲያኑ በሙሉ በጸሎት እንዲያስቧት አሳስቡልን። ምክንያቱም እርዳታውን የምታደርገው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ነው። የልቧን መሻት ይፈጽምላት ዘንድ በጸሎት አትርሷት።
•••
በእውነት ደስ ብሎኛል። እንዲህ ሰው ሲኖር ደስ ይላል። አሁንም ይቀጥላል። ቤተክርስቲያኑ በጣም ብዙ እርዳታ ይፈልጋል። ነገ በቪዲዮ በሰፊው እመጣለሁ። እስከዚያ ድረስ ግን በያላችሁበት Share በማድረግ ተባበሩን። እኔ በመጻፍ እናንተ Share በማድረግ ሌሎቹ በብር በመርዳት እንዲሁም በጸሎት በሃሳብ በመተባበር የእግዚአብሔርን ቤት እንሥራ። በዚህ ኑሮ 100 ብር ከካርድ ውጪ ምን ይሆናል? ለእግዚአብሔር ብትሰጡት ግን በረከቱ እጥፍ ድርብ ነው።
•••

አሁኑኑ ብር መላክ የምትፈልጉ ከሆነ
1000161193888 አገሬ ሁነኝ ሽቱ (AGERIE HUNEGN SHITU) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (
#የሽማጎ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ቤተክርስቲያን_አስተዳዳሪ_የሆኑት_የቀሲስ_መሐሪ_የባለቤታቸው_አካውንት_ነው

እኔን በቀጥታ ማግኘት ለምትፈልጉ
0910990644 (ዓምደ_ብርሃን)

"ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ የሰበሰብከው ገንዘብ ከህክምና አያልፍም! እግዚአብሔር የባረከልህ ድህነትህ ግን ጸጋ ነው!"


@AmdE_MeleK_13
በውስጥ ጻፉልኝ።