Get Mystery Box with random crypto!

ወገን ስለ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ምነው ዝምታን መረጣችሁ ? ለሥጋዊ ነገር ሲሆ | #የግጥም_ዓለም

ወገን ስለ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ምነው ዝምታን መረጣችሁ ? ለሥጋዊ ነገር ሲሆን እንፈጥናለን። ለመንፈሳዊ አገልግሎት ለምን እንዘገያለን። የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠራ እኮ እግዚአብሔር ነው። ለበረከት እንዲሁም ለድኅነተ ሥጋ ለድኅነተ ነፍስ ነው እንጂ! እግዚአብሔር ቤቱን ይሠራል። ከተሰጠን ላይ ብንሰጥ ችግር አለው? ካህናቱ ያለ ደመወዝ እያገለገሉ ነው። በኢኮኖሚ ደግሞ የገጠር አራሽ ቀዳሽ ናቸው። በእውነት እነዚህን ካህናት #መርዳት ነው ከጥያቄ የሚያድነን። በኋላ ብቸገር አልረዳችሁኝም ብሎ ነው ጌታ የሚጠይቀን።
•••

ምናልባት ዕድሉ ገጥሟችሁ ቦታውን ብታዩት ደስ ይለኝ ነበር። የእውነት ካህናቶቹ እንደ ጸጋ_ዘአብ ትሕትና ገንዘባቸው ነው። ቁጥራቸው 5 ቢሆኑም ፍቅራቸው ግን እልፍ ነው። የዛሬን አያድርገውና ሙሉ ጽጌን ከዚሁ ቤተክርስቲያን ነበር ያሳለፍኩት። እኛም እንግዳ ተብለን ለእኛ ብለው ድግስ ያዘጋጁ ነበር። በእውነት ከዚህ በረከት ተሳተፉ። እሽ ቢያንስ እንኳን ሃሳብ ስጡ። ለሌላ ነገር ከምንሯሯጥ ለሚጠቅመን እንሩጥ።

#ሽማጎ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሥዕለት_ሰሚው!