Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውጤት ካጣ በሆላ ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር Mulualem G. Medhi | Amde Ezra

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውጤት ካጣ በሆላ ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር Mulualem G. Medhin በ ያደረገረኩት አጠር ያለ ቆይታ ይህን ይመስላል፦

ሙሉዓለም፦ ወንድማለም ይሄው አንተ የአሰልጣኝነቱን ኃላፊነት ከተቀበልክ ጊዜ ጀምሮ ብሔራዊ ቡድኑ ከአገኘው ጋር እየተላተመ አያሌ ቀይ ካርድ እና ቢጫ ካርድ እየተሰጠው ነው ምንድን ነው ችግሩ?

አሰልጣኝ ውበቱ፦ ትክክል ነህ ሙሌ፣ ብዙ ችግር ነበረብን። ከካርድ በተጨማሪ በርካታ የቅጣት ምቶችም ተሰጠውብን ብዙ ተጎድተናል። ይችን ሦስት ቀን ግን ምንም ካርድ አላየንም፤ ቅጣት ምትም አልተመታብንም። ሰው ግን በዚች ሦስት ቀን ውስጥ ምን ያህል ቡድናችን ሰላም እንደሆነ አልተረዳልንም።

ሙሉዓለም፦ ይሄ ሰላም ከየት ነው የመጣው?

አሰልጣኝ ውብቱ፦ በርግጥ በዚች ሦስት ቀን ውስጥ ምንም ጨዋታ ስላልነበረን ነው።

ሙሉዓለም፦ እሺ ቡድኑ ከእፍሪካ ዋንጫ ውጪ እንዲሆን በማድረግህስ ከኃላፊነትህ አትለቅም ወይ

አሰልጣኝ ውበቱ፦ ለምንድን ነው የምለቀው? ጥያቄው መሆን የነበረበት 'ሁሉም የቡድኑ አባላት መልቀቅ አለባቸው፤ እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ኢሳያስ ጅራም መልቀቅ አለባት። የአትሌትክስ አሰልጣኝዋ ደራርቱ ቱሉም መልቀቅ አለባት፣ እሷም ብትሆን የሯጮች አለቃ ናት፤ ስፖርት ከተባለ ደግሞ ሁሉም ስፖርት ነው። ስለዚህም የቦክስ ፌድሬሽን አለቃም፣ የቼዝ ፌድሬሽን አለቃም መልቀቅ አለባቸው። ኃላፊነቱ የሁሉም ነው።

ነገር ዓለሙ ሁሉ 'ግንጊልቻ'

Mulualem G. Medhin