Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ማለት እንዲህ ናት... የማየት አቅሙ ያላችሁ ህጻኗን ተመልከቷት። እኔ ቪዲዮውን በእን | Amde Ezra

ኢትዮጵያ ማለት እንዲህ ናት...

የማየት አቅሙ ያላችሁ ህጻኗን ተመልከቷት። እኔ ቪዲዮውን በእንባ ነው የጨረስኩት። በጸጸት ነው የቋጨሁት። ሙሉውን ከፈለጋችሁ ከEBS ቴሌቪዥን ዩቱዩብ ገጽ ታገኙታላችሁ...

አባቷ ወታደር ነበር። "አገር ለማዳን" በሚል በጦርነቱ ተሰውቷል። በመጨረሻም የዳነው ሌላ ነው። "አገር ማዳን" የሚለው ያሁሉ ፕሮፖጋንዳ ማን እንደዳነ አውቀነዋል። እንኳን እንደ ዝች ምስኪን ህጻን አባት ደፋ ብለን አልቀረን። ተመስገን።

እንዳልኩት የህጻኗ አባት በጦር ሜዳ ተሰውቷል። የህጻኗ ወላጅ እናት ደግሞ በባሏ ሃዘን ጠዋት ማታ እየተወዘወዘች... እህህ... እያለች ባሏን ተከተለች። አርፋለች። የሞተችው ግን የዘጠኝ ዓመቷን ህጻን እና የሁለት ዓመት ጫቅላ ህጻኗን ትታ ነው። ያማል። ከዚህ በኋላ የዘጠኝ ዓመቷ ህጻን የሁለት ዓመት ወንድሟን ለመሳደግ ወደ ልምና ወጣች። የእናቷ እህትም አለች። እየለመነች በምታገኛት ገንዘብ በተደፋባቸው የቀን ጥላ ስር ይኖራሉ።

ኢትዮጵያ ግን የማናት? ለማነች? የአገር ባለውለታ ልጆች እንዲህ ሆነዋል። ሌላው ደግሞ ጠግቦ ሲተፋ ያድራል። "አገር ለማዳን ተነሱ" ያሉት ባለስልጣናት ናጥጠዋል። በእርግጥ ይች ህጻን እድለኛ ሆና በካሜራ ዕይታ ወስጥ ገባች እንጂ በዚህ ጦርነት የስንቱ የሞቀ ቤት ፈርሷል መሰላችሁ። ስንት ህጻናት ተበትነዋል መሰለችሁ። ኢትዮጵያ ማለት እንዲህ ናት። የሸጣት የሚዘባነንባት፣ የሞተላት ደግሞ ዳግም የሚሞትባት።

ይችን ህጻን ለማገዝ የምትፈልጉ ካላችሁ አድራሻዋን ከEBS ቴሌቭዥን ልታገኙ ትችላላችሁ...