Get Mystery Box with random crypto!

የልማት አርበኛው ገዳም 'ማን እንደ አባአቡነ ያሳይ' አንድነት ገዳም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ም | Amde Ezra

የልማት አርበኛው ገዳም "ማን እንደ አባአቡነ ያሳይ" አንድነት ገዳም

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደምቢያ ወረዳ የምትገኘው ጎርጎራ የጣና ሐይቅ ወደብ ከመሆኗ ባሻገር በደሴቶቿና በዳርቻዋ በርካታ ገዳማትን አቅፋ የያዘች ናት።

ለአብነትም ደብረ ሲና ማርያም፣ ማን እንዳባ መድኃኔ ዓለም፣ ብርጊዳ ማርያም፣ ገሊላ ኢየሱስ፣ አንጋራ ተክለ ሃይማኖት፣ እጅ በራ ማርያም እና ሌሎችም ገዳማቶች ከበዋት ይገኛሉ፡፡

"ማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ" አንድነት ገዳም በርካታ መነኮሳቶች ያሉት ሲሆን በእንስሳት እርባታ፣ በንብ ማነብ እና በግብርና ስራዎች የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል።

ኢትዮጵያ አቅፋ የያዘቻቸው፣ ጠብቃ ያኖረቻቸው አያሌ ሚስጥራት አሏት፡፡ እነዚያ ሚስጥራትም የዓለም ሚስጥር መፍቻ ቁልፎች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ግን ሚስጥር ናት፡፡ ገዳሙን ይዩት፤ ይጎብኙት፣ ይረኩበታል፤ መልካም ነገርም ያገኙበታል::

በመሆኑም ዓመታዊ የንግስ በዓሉ የፊታችን መጋቢት 27/2015 በደመቀ ሁኔታ ስለሚከበር የበዓሉ ተሳታፊ በመሆን በረከትን ያግኙ፡፡

መረጃው የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን ነው።