Get Mystery Box with random crypto!

ሕወሓት ጥቃት በማቆም ወደ ምክክር እንዲመጣ ሲል መንግሥት አሳሰበ አምባ ዲጂታል፤ ሐሙስ ነሐሴ 1 | Amba Digital - አምባ ዲጂታል

ሕወሓት ጥቃት በማቆም ወደ ምክክር እንዲመጣ ሲል መንግሥት አሳሰበ

አምባ ዲጂታል፤ ሐሙስ ነሐሴ 19፣ 2014 ― ሕወሓት እየፈፀመ የሚገኘውን ጥቃት በማቆም ወደ ምክክር እንዲመጣ ሲል መንግሥት ያሳሰበው በዛሬው እለት ማለትም ነሐሴ 19፣ 2014 ባወጣው መግለጫ ነው።

በመንግሥት ኮሚኒኬሽን በኩል በወጣው መግለጫ፤ ሕወሓት ይህን ጥሪ የማይቀበል ከሆነ መንግሥት ሀገራዊ ሉአላዊነትንና የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።

ለአምስት ወራት ያህል ጋብ ብሎ የቆየው የፌዴራል መንግስት እና ሕወሓት ጦርነት ትላንት ዳግም መጀመሩ ይታወቃል።

ጦርነቱን ማን ጀመረው በሚለው ላይ ሁለቱም አካላት አንዳቸው ሌላኛውን እየወነጀሉ ይገኛል።

የፌዴራል መንግስት እና ሕወሓት ጦርነት ዳግም ያገረሸው ለድርድር ይቀመጣሉ ተብሎ በተጠበቀበት ሰዐት ነው።

https://ambadigital.net/2022/13845/