Get Mystery Box with random crypto!

#መስራት_ካቃተህ_5ቱን_አድርግ! #1ኛ_ስልክህን_አጥፋ ስራ ለመስራት ተቀምጠህ በተቀመጥክበት የ | AbrshDREAMS

#መስራት_ካቃተህ_5ቱን_አድርግ!

#1ኛ_ስልክህን_አጥፋ

ስራ ለመስራት ተቀምጠህ በተቀመጥክበት የኖቲፊኬሽን መዓት ይገባልሀል። መጀመሪያ ትንሽ ትሰራና ስልክህን ትጎረጉራለህ፤ አሁንም ትንሽ ቆይተህ እንደዛው፤ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ስራውን ትተህ ስልክህ ላይ ተጥደሀል። የስራው ጊዜ ገደብ አልቋል፤ ነገር ግን ስራው አልተሰራም። ይኼ አጋጥሞህ የሚያውቅ ከሆነ፣ መፍትሄው ስልክህን አጥፍተህ፣ ከራስህ አርቀህ ማስቀመጥ ነው።

#2ኛ_አካባቢ_ቀይር

አካባቢያችን ስራችን ላይ ተጽኖ ያሳድራል። ለምሳሌ ቆሻሻ አካባቢ የተረጋጋ አእምሮ አይፈጥርም፤

መኝታ ቤት ለእንቅልፍ ይጋብዛል።

ግርግር ያለበት ቦታ ትኩረትህን ይሰርቃል። ስለዚህ ንጹህ፣ ጸጥታ ያለበትና ለስራው ምቹ ወደ ሆነ ቦታ ከቀየርክ የተሻለ ስራ ትሰራለህ።

#3ኛ_የሚረዳህን_ሰው_ፈልግ

ስራው ካስቸገረህ የስራ ሞራልህም ይሞታል። በስራው ከአንተ የተሻለ ሰው ፈልገህ እንዲረዳህ ብትጠይቀው ችግርህ ይቀረፋል።

#4ኛ_እረፍት_አድርግ

በቂ እረፍት አለማድረግ ስራህ ላይ ጫና ያደርሳል። እንቅልፍ ማጣት፣ በቂ የአካልና የአእምሮ እረፍት አለማድረግ ለስንፍናህ መንስዔ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ እረፍት አድርግ፣ ተኛ፤ የሚያዝናናህን ነገር አድርግ ከዚያ ወደ ስራህ ተመለስ።

#5ኛ_አነቃቂ_ጽሑፎችን_አንብብ

ስንፍና ሲጫጫንህ አንተን ለማነቃቃት የተጻፉ አነቃቂ ጽሑፎች እና ቪዲዮዎች ተከታተል፤ ስንፍናህን አባሮ በአዲስ ተነሳሽነት ይሞላሀል።

የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM